1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶስቱ ትላልቅ ሀይማኖቶች በጀርመን

ማክሰኞ፣ መስከረም 7 2000

Weißt du wer ich bin ?ማንነቴን ታውቃለህ?

https://p.dw.com/p/E0bx
የሶስቱ ታላልቅ ሀይማኖቶች የዕምነት ምልክቶች
የሶስቱ ታላልቅ ሀይማኖቶች የዕምነት ምልክቶች

በጀርመን የሶስቱን ትላልቅ ሀይማኖቶች ተከታዮች ለማቀራረብ ከሚደረጉት ሙከራዎች ውስጥ ማንነቴን ታውቃለህ? በተሰኘው ፕሮጀክት ስር የሚከናወኑት ተግባራት ይገኙበታል።
ይኽው ፕሮጀክት በጀርመን የክርስትና የእስልምናና የአይሁድ ዕምነት ተከታዮች በራቸውን ዘግተው ከመኖር ይልቅ እንዲቀራረቡና ሰላማዊ ህይወት እንዲመሩ የየሀይማኖቶቹን መሪዎችና የዕምነቱን ተከታዮች ያደፋፍራል። በዚህ ሂደት የሚገኘው የልምድ ልውውጥም በጀርመን የተለያየ ዕምነት ተከታዮች ይበልጡን አብረው በሰላም እንዲኖሩ አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ዕምነት አለ። ግቡ በጀርመን የሶስቱ ዋና ዋናዎቹ ሀይማኖቶች መሪዎችና ተከታዮች እንዲወያዩና እንዲቀራረቡ ልምድም እንዲለዋወጡ ማድረግ ነው።

መነጋገር ፣ ለችግሮች የጋራ መፍትሄ መሻትና አንዱ ለሌላው ዕምነት አክብሮት እንዲሰጥ የአምልኮ ስፍራዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘት በፕሮጀክቱ ውስጥ የተካተቱ ዕንቅስቃሴዎች ናቸው። የሶስቱ ሀይማኖቶች ተከታዮች በጋራ የሚሳተፉበት ጉባኤም ሌላው የፕሮጀክቱ አካል ነው ። የፕሮጀክቱ ሀላፊ ካሪን ኩላ።
ዓላማው በጀርመን በሰላምና በአንድነት መኖርን ይበልጥ ማጠናከር ነው። ይህ አንዱ በጣም ትልቁ ግብ ነው ። በዚህ ሂደትም እንደ ማንኛውም ሰው ርስ በርስ እንገናኛለን ።በህይወት ውስጥ ትልቅ ግምት ስለምንሰጠው ነገር እንነጋገራለን ፤ ከሰዎች ጋር እንተዋወቃለን ፤ በዚህ ወቅትም ራሴንም አውቃለሁ።
ወይዘሮ ኩላ እንደሚሉት የሚነጋገር ወደ ጠብ አያመራም። ከተቃራኒው ጋር ሀሳብ የሚለዋወጥ በሌላው ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል። ከዚሁ መሰረተ ሀሳብ በመነሳትም ከሶስት ዓመታት አንስቶ የካቶሊክ የኢቫንጀሊካልና የኦርቶዶክስ እንዲሁም የነፃው ክርስትቲያኖች አብያተ ክርስትያናት እንዲሁም በጀርመን የሚኖሩ አይሁዶች እና ሙስሊሞች በጋራ የሚገናኙባቸውን መድረኮች ፕሮጀክቱ አመቻችቷል። ይህም እንደ ወይዘሮ ኩላ አንዱ ሰለሌላው እንዲያውቅ ብቻ ሳይሆን ከሌላው እንዲማርና ማንነቱንም እንዲያገኝ ይረዳል ።

ታዲያ የልዩ ልዩ ዕምነት ተከታዮችን ለማቀራረብ በሚደረገው ሙከራ የሀይማኖት መሪዎች ሚና ከፍ ያለ ነው። በውይይቶች ላይ የሚነሱ ሀሳቦችን በአሳማኝ መልኩ ማቅረብ ከነርሱ ይጠበቃል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በጀርመን የሚገኙ የልዩ ልዩ የሀይማኖት መሪዎች በርስ በር ግንኙነቱ አማካይነት ምዕመናን ወደ ሌላ ዕምነት እንዳይሄዱ ያደረባቸው ፍራቻ ማስወገድ ይኖርባቸዋል። እነዚሁ የሀይማኖት አባቶች በሌላው ወገን ላይም ዕምነት ሊያድርባቸው ይገባል። ሙስሊሞችና አይሁዶችን ለማቀራረብ መጀመሪያ ላይ ችግር ነበር። በጀርመን ትልቁ የቱርክ ሙስሊሞች ማህበር እና የአይሁዶች ማዕከላዊ ምክርቤት ከዚህ ቀደም በቅርብ ተባብረው አያውቁም። መጀመሪያ ላይ የውይይት መድረኩን ጥሎ ለመውጣትም አስበው ነበር። ሆኖም ግን በመጨረሻ ለችግሩ ገንቢና ዘላቂ መፍትሄ አግኝተናል።


ማንነቴን ታውቃለህ ከተሰኘው ፕሮጀክት ጎን ለጎን በርካታ አጋዥ ፕሮጀክቶችም ይካሄዳሉ። በተለያዩ ከተሞች የሚካሄዱ ሀይማኖቶች ላይ ያተኮሩ ስብሰባዎችም በዚህ ረገድ ይጠቀሳሉ። ሃሉክ ይልዲዝ ቦን የሚገኙ መስጊዶችና የሙስሊም ተቋማት ምክርቤት ቃል አቀባይ ናቸው ። በዋናዋናዎቹ ሀይማኖቶች መካከል የተጀመረው ቅርርብ በጎ መሆኑን ነው የሚናገሩት። ተለመከቱ መድረኩ ላይ ተቀምጠን ከናንተ ፊት እየተነጋገርን ነው። እናንተም ስንነጋገር እየተመለከታችሁን ነው። እንዴት እንደምንወያይ ስለምን እንደምንወያይ እያያችሁ ነው ። ይህ ደግሞ የህዝቡም ጥያቄ ነው ። ህዝቡም ከዚህ ብዙ ይቀስማል ። የዚህ አስተሳሰብ መንፈሱና ዓላማው ይኽው ነው።