1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሸገር 102.1 ኤፍ ኤም

ረቡዕ፣ ጥቅምት 15 2010

ለየት ባለ አቀራረቡ ተደማጭነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የሚነገርለት የራድዮ ጣቢያው መሥራች እና ባለቤት ወይዘሮ መዓዛ ብሩ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የስኬታቸው ሚስጥር አማራጭ ሆነው መቅረብ መቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/2mVLa
10 Jahre Sheger FM Äthiopien
ምስል DW/G. Tedla

ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ 10ኛ ዓመት


ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ የተመሠረተበትን አሥረኛ ዓመት ትናንት በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ አክብሯል። ለየት ባለ አቀራረቡ ተደማጭነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የሚነገርለት የራድዮ ጣቢያው መሥራች እና ባለቤት ወይዘሮ መዓዛ ብሩ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የስኬታቸው ሚስጥር አማራጭ ሆነው መቅረብ መቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ ቀለል ባለ አቀራረብ እያዝናኑ በሚያስተምሩ ዝግጅቶቹ ይበልጥ ሳቢ መሆን መቻሉን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ