1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሹማኽር የደረሰበት አደጋ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 21 2006

የጀርመን መራሄ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጀርመናውያን ሹማኽር በደረሰበት አደጋ ድንጋጤያቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው ።

https://p.dw.com/p/1AihW
ምስል AP


« ፎርሙላ 1» በተሰኘው ፈጣን የአውቶሞቢሎች እሽቅድምድም ሰባት ጊዜ የዓለም ሻምፕዮን ጀርመናዊው ሚካኤል ሹማህር ትናንት በደረሰበት አደጋ ጀርመናውያን ተደናግጠዋል ። በፈረንሳዩ የአልፕስ ተራራ ትናንት በበረዶ ላይ ሲንሸራተት ራስ ቅሉ ላይ በደረሰበት አደጋ ክፉኛ መጎዳቱንና በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሃኪሞች ተናግረዋል ። የጀርመን መራሄ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጀርመናውያን ሹማኽር በደረሰበት አደጋ ድንጋጤያቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የበርሊን ነዋሪዎችን አነጋግሮ ቀጣይን ዘገባ ልኮልናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ