1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሻርማርኬ ስልጣን ለቀቁ

ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2003

የመልቀቂያ ደብዳቤአቸውን ለፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ሰጥተዋል። በፕሬዝዳንቱና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መኃል የተፈጠረው አለመግባባት መጨረሻው የሻርማርኬ መልቀቅ ሆነ።

https://p.dw.com/p/PIHv
ጠቅላይ ሚኒስትር ሻርማርኬምስል AP

ትላንት፤ በአክራሪ እስላማዊ ኃይሎች ላይ የተጠናከረ ዘመቻ ለመክፈት መንግስታቸው መዘጋጀቱን መግለጻቸው ተሰማ። ዛሬ፤ ከያዙት ሥልጣን በፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተነገረ።በጠቅላይ ሚኒስትር ዑመር አብዲረሽድ ዓሊ ሻርማርኬና በፕሬዝዳንት አህመድ ሻሪፍ መኃል የተፈጠረው አለመግባባት ዛሬ በስልጣን መልቀቂያ ፊርማ ለየለት። የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የሶማሊያ ወኪል ጋዜጠኛ ሙስጠፋ ሀጂ አብዲኑር እንደሚለው የሻርማርኬ መልቀቅ ባለፈው ሳምንት የፈነዳው የሁለቱ መሪዎች ጸብ ውጤት ነው። ሶማሊያ እንዲህ በቀውስ እየታመሰች ባለችበት በዚህን ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ሻርማርኬ የመልቀቅ ዜና ብስራት ይሁን መርዶ፤ በእርግጥ አለየለትም። በዓለም አቀፉ የግጭት አጥኚ ቡድን የሶማሊያ ተንታኝ ረሺድ አብዲ የሻርማርኬ መልቀቅ ብዙም ትርጉም የለውም ይላሉ።