1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

‘ሽኖዬ’ ባህላዊ የልጃገረዶች የአዲስ ዓመት ጫወታ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 5 2013

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ስያሜዎች ይታወቃል፡፡ ሽኖዬ፣ አባቢሌ እና ሌሎችም መጠሪያዎች ታዳጊ እና ያላገቡ ወጣት ሴቶች በአዲስ ዓመት መግቢያ ላይ ተሰባስበው የሚጫወቱት ባህላዊ ጭፈራ ነው፡፡

https://p.dw.com/p/40Ae0
Äthiopien | Neujahrsfest | Shinoye Spiel
ምስል Seyoum Getu/DW

ዝግጅቱ ባህሉን ከመጥፋት ለመታደግ የሚጥሩ ወጣቶችን እንግዳዉ አድርጎአል

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ስያሜዎች ይታወቃል፡፡ ሽኖዬ፣ አባቢሌ እና ሌሎችም መጠሪያዎች ታዳጊ እና ያላገቡ ወጣት ሴቶች በአዲስ ዓመት መግቢያ ላይ ተሰባስበው የሚጫወቱት ባህላዊ ጭፈራ ነው፡፡

በዚህ ባህል ሴት ልጃገረዶቹ እርሰበርስ እና በዓመቱ ምናልባትም በጋብቻ አሊያም በሞት ከመሃላቸው ያጡትን ጓደኛቸውን ስም ጠርተው ከፍ አድርገው የሚያሞግሱበትም ነው፡፡

ይህ የወጣቶች ዝግጅት ባህሉን ከመጥፋት ለመታደግ ከመጣር ጎን ለጎን ባህሉን ምክኒያት በማድረግ እየጨፈሩ እና በማህበራዊ መገናኛ ዘመቻ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አጥተው ለሚቸገሩ ሴት ተማሪዎች የማሰባሰብ ዓለማን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ወጣት ሴቶች እንግዳው አድርጓል፡፡

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ