1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለምልልስ ጌታቸው ተድላ/ከንቲባ አርከበ እቑባይ(1)

ሐሙስ፣ ጥቅምት 18 1997

በ፫ኛው ዓለም ውስጥ ገጠሬው ሕዝብ የተሻለ የኑሮ ዕድል የሚያገኝ እየመሰለው፥ ከየመኖሪያ ቀዬው እየተፈነቃቀለ ወደ ከተሞች የሚሸሽበት ሁኔታ ዛሬ ኢትዮጵያም ውስጥ በተለይም በርእሰከተማይቱ አዲስ አበባ አኳያ በየጊዜው እየጎላ የሚሄድ ድርጊት ሆኗል።

https://p.dw.com/p/E0fG

የከተማ ሠፈሮች መተፋፈግና መጎሳቆል፣ የመኖሪያ-ቤቶች እጥረት፣ የንጽሕና ጉድለት እና የሥራ አጦች ብዛት ነው ዛሬ አዲስ አበባን የሚያስጨንቀው። የአፍሪቃም መዲና ስለሆነችው ስለዚህችው ከተማ ችግሮች መፍትሔና ዕድገት ወኪላችን ጌታቸው ተድላ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ የምሥጉን አስተዳደርን መርሕ ለማራመድ ይጥራሉ ከሚባሉት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ከሆኑት ከአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ አርከበ እቑባይ ጋር ሰሞኑን ቃለምልልስ አካሂዶ ነበር። በዛሬው “የኤኮኖሚው ዓለም” መርሐግብር ክፍለጊዜአችን፣ የዚሁኑ ቃለምልልስ መጀመሪያ ከፊል የምናሰማችሁ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ሣምንት የምናቀርብላችሁ ሁለተኛው ከፊል ደግሞ በንግዱ ኅብረተሰብእ ኣኳያ ስለተቀረፁት መመሪያዎች እና በዲሱ የብሔራዊ ግንባታ አሠራር መሠረት ነባሮቹ ባለርስት ነዋሪዎች ማካካሻ እንዲሰጣቸው በሚያቀርቡት ጥያቄ ላይ የሚያተኩር ይሆናል።