1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ መጠይቅ፤ የእርስ በርስ ጦርነት ጥፋቱ፣ መንስኤና መፍትሔዉ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2014

አሁን ሐገሪቱንና ሕዝቡን የሚያጠፋዉ ጦርነት፣ የጎሳ ግጭትና ጥላቻን ለማስወገድ የሐገሪቱ ምሁራን የችግሩ አካል በመሆናቸዉ መፍትሔ ያመጣሉ ወይም ይጠቁማሉ የሚል ተስፋ የላቸዉም።

https://p.dw.com/p/42BiD
Bayisa Wak-Woya | ehemaliger UN Repräsentant
ምስል Privat

ከአቶ ባይሳ ዋቅወያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

አቶ ባይሳ ዋቅወያ  የዓለም አቀፍ ሕግ ምሁር ናቸዉ።እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1989 ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ሆነዉ  በሰሩባቸዉ ከአፍቃኒስታን እስከ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ የተደረጉ የእርስበርስ ጦርነትና ግጭቶችን በቅርብ ተመልክተዋል።የየግጭት-ጦርነቶቹን መነሻ፤ ያደረሱትን ጥፋትና መፍትሔያቸዉንም ተንትነዋል።«በርስበርስ ጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለም» ይላሉ።ሰዉ አንዴ ወገኑን መግደል ከጀመረ ደግሞ፣ አቶ ባይሳ እንደሚሉት ባጭር ጊዜ ወደ «አዉሬነት» ይቀየራል።

አቶ ባይሳ እንዳሉት የኢትዮጵያ ልሒቃን «ዕብደት» ከጀመሩ 50 ዓመት ሆኗቸዋል።አሁን ሐገሪቱንና ሕዝቡን የሚያጠፋዉ ጦርነት፣ የጎሳ ግጭትና ጥላቻን ለማስወገድ የሐገሪቱ ምሁራን የችግሩ አካል በመሆናቸዉ መፍትሔ ያመጣሉ ወይም ይጠቁማሉ የሚል ተስፋ የላቸዉም።ያም ሆኖ  ጦርነት እና ግጭቱን ለማስወገድ «ከድርድር ሌላ አማራጭ የለም» ባይናቸዉ።አቶ ባይሳን በስልክ አነጋግረናቸዋል።ሙሉ ቃለ ምልልሱን ያድምጡ፣-

ነጋሽ መሐመድ