1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቅድመ-ብይን እና ፍራቻ

ዓርብ፣ የካቲት 13 2007

የኢቦላ በምዕራብ አፍሪቃ መቀስቀስና በፍጥነት መስፋፋት አብዛኛውን ጊዜ ተጨባጭ ባልሆኑ፥ ሊቀለበሱ በማይችሉ ቅድመ-ብይኖች እና ፍራቻዎች የታጀበ ነው።

https://p.dw.com/p/1Ef4I
Ebola Jahr 2000 Gulu Uganda Helfer
ምስል Getty Images/Carlos Palma/AFP

ቅድመ-ብይን፦ኢቦላ ያለበትን ሰው ባገኝ ወዲያውኑ ኢቦላ ይይዘኛል።

መልስ፦ስህተት።የኢቦላ ተሐዋሲ አየር ወለድ አይደለም። ኢቦላ ሊተላለፍ የሚችለው በኢቦላ ተሐዋሲ የተነሳ ከታመመ ሰው ጋር የደም አለያም የሰውነት ፈሳሽ ንክኪ ከተፈጠረ ብቻ ነው። ብዙ ሰዎች እጅግ አስፈሪ ፊልሞችን በተደጋጋሚ የሚመለከቱ ከመሆናቸው አንፃር ተሐዋሲው ገዳይ ነው የሚለው አመለካከት ተስፋፍቷል። ምንም እንኳን በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢቦላ መሞታቸው እሙን ቢሆንም ሌሎች እንደ ኢንፍሉዌንዛ ያሉ ተሐዋስያን ግን ከዛም በፈጠነ መልኩ ነው የሚሰራጩት።

ቅድመ-ብይን፦ኢቦላን በመዋጋት ማሸነፍ አይቻልም

መልስ፦በርካታ ባለሙያዎች የኢቦላ ተሐዋሲ በዓለም አቀፍ ጥረት በቁጥጥር ስር ሊውል ይችላል የሚል እምነት አላቸው፤ በእርግጥ እስከዚያ ድረስ ጥቂት ወራቶችን ሊወስድ ቢችልም ማለት ነው። ክትባቶች ሙከራ እየተደረገባቸው ነው። ጥቅም ላይ የመዋላቸው ነገር የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው።

ቅድመ-ብይን፦ኢቦላን የፈጠሩት ምዕራባውያን ናቸው

መልስ፦ይኽን መላምት ለመደገፍ ተጨባጭ መረጃ የለም። ኢቦላ በቅድሚያ የተገኘው እጎአ በ1976 በአውሮጳውያን ሣይንቲስቶች ነው፤ ሆኖም ተሐዋሲው ከዚያን ጊዜ ቀደም ብሎም በመካከለኛው አፍሪቃ እና ደቡብ ምሥራቅ እስያ ጥቅጥቅ ደኖች ውስጥ ይኖር እንደነበር ተመራማሪዎች ያምናሉ።

ቅድመ-ብይን፦ ከኢቦላ መዳን ይቻላል

መልስ፦እስካሁን ድረስ እውቅና የተሰጠው የኢቦላ መድሐኒት የለም። ኢቦላን ሌሎች መሠረታዊ የሚባሉ ነገሮችን በመጠቀም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ብቻ ማከም ይቻላል። የኢቦላ ታማሚን በቀጥታ አክሞ ለማዳን የሚያስችሉ መድሐኒቶች በሙከራ ላይ ናቸው። ራሳቸውን ተዓምረኛ ብለው የሠየሙ መድሐኒት አዋቂዎች ኢቦላን ሊያድኑ እንደሚችሉ አስረግጠው ይናገራሉ፤ ይሁንና ግን የሚጠቀሙባቸው የሕክምና ዘዴዎች በአጠቃላይ እጅግ አደገኛ ናቸው። ሴራሊዮን ውስጥ አንዲት ባሕላዊ መድሐኒት አዋቂ ኢቦላን ማዳን እችላለሁ ካሉ በኋላ ተሐዋሲው የበለጠ እንዲስፋፋ ሰበብ በመሆናቸው ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎች ሊሞቱ ችለዋል።