1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በላይ ዘለቀ «አባ ኮስትር በላይ»

ሐሙስ፣ ሰኔ 7 2004

ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮያን እንደወረረች ፤ 5 ዓመት በዱር በገደል ፣ በተለይ በጎጃም ክፍለ ሀገር ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ ተደጋጋሚ ድል ከተቀዳጁትና ለነጻነት መመለስ ታላቅ ድርሻ ካበረከቱት የኢትዮጵያ ስመ ጥር አርበኞች መካከል አንዱ ፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ናቸው።

https://p.dw.com/p/15Dl8
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

«እስቲ፣ በስማም ብዪ ልጀምር፣ ሰላምታ

አባ ኮስትር በላይ የሃይማኖት ጌታ።

እስቲ በስማም ብዪ ልጀምር ታምር

አባ ኮስትር በላይ የጦር ሚኒስትር»

ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮያን እንደወረረች ፤ 5 ዓመት በዱር በገደል ፣ በተለይ በጎጃም ክፍለ ሀገር ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ ተደጋጋሚ ድል ከተቀዳጁትና ለነጻነት መመለስ ታላቅ ድርሻ ካበረከቱት የኢትዮጵያ ስመ ጥር አርበኞች መካከል አንዱ ፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ናቸው። ባለፍዉ ሰምወን የበላይ ዘለቀን 100 ኛ አመት በማስታወስ የተለያዩ የታሪክ አዋቂዎች፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር አባላት፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች በተገኙበት ዝግጅት ተካሂዶዘል።

«እንደ ሰለሞን እንደ ሲራክ

እንደ ደጉ ንጉስ እንደ ሚኒሊክ

መች ተጥፎ ያልቃል የኮስትር ታሪክ»

ደጃዝማች በላይ ዘለቀ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ ድርሻን ያበረከቱ ናቸዉ። እዚህ በጀርመን ሃንቡርግ ከተማ በሚገኘዉ ዩንቨርስቲ እ,ጎ,አ በ2003 ዓ,ም በተካሄደዉ በ15 ኛዉ አለማቀፍ የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤ ላይ ስለ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት በሃንቡርግ ዩንቨርቲ የአፍሪቃ የኢትዮጵያ ጥናቶች ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ጌቲ ገላይ፤ ስለ በላይ ዘለቀ ያሰባሰቡትን ጥናታዊ ጽሁፍ ለአንባብያን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ናቸዉ። በለቱ ዝግጅታችን በበላይ ዘለቀ ታሪክ እና በጀግንነታቸዉ ዙርያ የሚነግሩትን ስነ-ቃሎች ይዘን ባለሞያዎች አነጋገረን ቅንብር ይዘናል መልካም ቆይታ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ