1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመቅዲሾ ሰላማዊ ሰልፍ/ የዩኤስ ወታደሮች አፈና

ሐሙስ፣ ጥር 24 1999

በመቶ የሚቆጠሩ ሶማልያዉያን ዛሬ በዋና ከተማዋ መቅደሾ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። በሶማልያ በተለያየ ቦታ በኢትዮጽያ የሚደገፈዉ የሽግግሩ መንግስት የጦር ሃይላት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት በመድረስም ላይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/E0Yn
ሰላማዊ ሰልፍ በመቅዲሾ
ሰላማዊ ሰልፍ በመቅዲሾምስል AP

በሌላ በኩል በደቡብ ሶማልያ በእስላማዉያኑ የተማረኩ አስራ አንድ የአሜሪካ ወታደሮችን ለማስለቀቅ የአሜሪካዉ አምባሳደር በኬንያ Michael Ranneberger እና በኬንያ መንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙት የሶማሌ እስላማዊ ህብረት መሪ Sheik Sharif Sheik Ahmed ድርድር እንደያዙ የሸበሌ የዜና ወኪል በድረ-ገጹ ይፋ አድርጎዋል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ በመቅዲሾ ነዋሪ የሆነዉ ጋዜጠኛ ዩሱፍ አዊስን አዜብ ታደሰ አነጋግራዉ ነበር ።