1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመቐለ ሕገ ወጥ የመሬት ቅርምትና ሥራ አጥነት

ሰኞ፣ መጋቢት 23 2011

በመቐለ ዙርያ የሚገኙ አርሶ አደሮች ያለ ተመጣጣኝ ካሳ ከቅያቸው በመነሳታቸው ለከባድ ኢኮኖምያዊና ማሕበራዊ ችግር እየተጋለጡ መሆናቸው ተነገረ፡፡ ለኢንቨስትመንት ለመሠረተ ልማት ለቤቶች ግንባት በሚል ምክንያቶች ከተማዋ ያላግባብና ያለ ሕግ ወደ ጎን መስፋት ብቻ ሳይሆን ለገበሪዎች የሚሰጣቸዉ ካሳም ዝቅተኛ በመሆኑ ችግሩን አባብሶታል ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/3G2yO
Äthiopien Mekele-Bauern und Studenten reichen Beschwerden ein
ምስል DW/M. Haileselassie

በመቐለ ዙርያ የሚገኙ አርሶአደሮች ያለ ተመጣጣኝ ካሳ ከቅያቸው በመነሳታቸው ለከባድ ኢኮኖምያዊና ማሕበራዊ ችግር እየተጋለጡ መሆናቸው ተነገረ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች የአስተዳደርና ስራ ዕድል ፈጠራ ጥያቄዎች በመቐለ ከተማ ወጣቶች እየቀረቡ እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ዓመታት የትግራይ ክልል ርእሰ ከተማ የሆነችው መቐለ ወደ ጎን እየሰፋች መምጣትዋ ተከትሎ በዙርያዋ ይኖሩ የነበሩ አርሶአደሮች ከማሳቸው እየተነሱ ለከባድ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማሕበራዊ ችግር እየተጋለጡ መምጣታቸው ይገለፃል፡፡ ይህና ሌሎች ችግሮች መነሻ በማድረግ ከሁለት ሺህ በላይ የሚገመቱ የመቐለ ኩሓ ክፍለከተማ ወጣቶችና አርሶአደሮች ለመንግስት ጥያቄዎቻቸው በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ ከመሬት ጉዳይ በተጨማሪ ወጣቶች የመልካም አስተዳደር፣ ተጠቃሚነት እንዲሁም በአካባቢያቸው ሰው የመተዳደር ጥያቄዎች ያቀርባሉ፡፡ ወጣቶቹ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ የአርሶአደሩ የካሳ ጉዳይ በትኩረት እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ