1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመተከል ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎች ተገደሉ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 6 2014

በቤኒሻል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን  ድባጢ ወረዳ ጋለሳ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ ። ባለፉት ጥቂት ቀናት  በታጣቂዎቹ በደረሰው ጥቃት በርካቶች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። የዞኑ የጸጥታ ዕዝ በበኩሉ የጥቃቱን መፈጸም አረጋግጦ ለጥቃቱ ኦነግ ሸኔ የተባለውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/41led
Karte Äthiopien Metekel EN

በመተከል ዞን የታጣቂዎች ጥቃት እና የደረሰው ጉዳት

በቤኒሻል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን  ድባጢ ወረዳ ጋለሳ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ ። ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደገና አገርሽቶ  በታጣቂዎቹ በደረሰው ጥቃት በርካቶች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። የዞኑ የጸጥታ ዕዝ በበኩሉ የጥቃቱን መፈጸም አረጋግጦ ለጥቃቱ ኦነግ ሸኔ የተባለውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርጓል። በዞኑ የተለያዩ ክልሎች ልዩ ሀይሎች በጸጥታ  ማስከበር ስራ ተስማርተዋል ተብሎ በመንግስት ከተገለጸ ሳምንታትን ተቆጥረዋል፡፡በጋለሳ ቀበሌ የሚገኝ መሰረተ ክርቶስ ቤተክርስቲያን   በበኩሉ በጋሌሳ ከተማና በገጠር ቀበሌዎች በሚገኙ ተቋማቱ ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክቷል፡፡ ከአስር በላይ የነዋሪዎች ቤት መቃጠሉንም ገልጿል፡፡ የዞኑንኑ የጸጥታ ጉዳይን በበላይነት ከሚመሩት በጉዳዩ ላይ በሰጡን ማብራሪያ በስፋራው ሰሙኑን የአራት ሰዎችቸን ህይወት ያጠፉት የሸነ ታጣቂዎች ናቸው ያሉ ሲሆን ከታጣቂዎች ግንኑነት አላቸው የተባሉ ሚሊሻች እና ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ የጸጥታ ችግር የሚስዋልበት አካባቢ ተብሎ በኮማንድ ፖስት መጠበቅ የጀመረው መተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚፈጠሩት ጥቃቶች ምክንያት በንብረትና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል፡፡ በዞኑ ድባጢ ወረዳ ጋሌሳ ቀበሌ ከሳምንት በፊት  በርካታ ሰዎች  በአካባቢው ሰላም ለማስፈን በስራ ላይ በሚገኘው የጸጥታ ሀይሎች መታሰራውን ነዋሪዎቸች  ገልጸዋል፡፡  ከትናንት በስቲያ ደግሞ በድጋጢ ወረዳ ጋሌሳ ቀበሌ ውስጥ አራት ሰዎች ህይወት ማለፉን  ነዋሪዎች ለዲደቢሊው ተናግረዋል፡፡

በድባጢ ወረዳ ጋለሳ  ቀበሌ  የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክስቲያ አገልጋይ መሆናቸውን የነገሩንና በስፍራው ባለው የጸጥታ ችግርም ምክንያት  ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ   በተቋማቸው ላይ ጉዳት መድረሱን፣ እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችም መውደማቸውን  ተናግረዋል፡፡ ከመስከረም 17 አንስቶ በስፍራው ተደጋጋሚ ጥቃቶች መድረሳቸውን እና ጥቅምት 3 /2014 ዓ/ም በቀበሌው በጸሎት ላይ በነበሩ ምእመናን ላይም ጉዳት መድሩሱንም ነግሮናል፡፡  በቀበሌው 13 ሰዎች መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውንም አብራርተዋል፡፡በስፍራው የተሰማራው የጸጥታ ሀይሎች ከሸማቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት የነዋሪውን ቤቶች ማቃጠላቸውንም ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡  

የነዋሪውን ቅሬታ አስመልክቶ ምላሽ እንደሲጡን ከዞኑ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴነሮ በጋሌሳ ጉዳት ያደረሱት  በአካባቢው ይንቀሳቀሳለው  የተባሉ የሸኔ ሸማቂዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ የአራት ክልሎች ልዩ ሀይሎች መሰማራታቸውንና ከሰላም ማስከበር ስራ ውጭ በነዋሪው ላይ ያደረሱት ጉዳት የለም ብለዋል፡፡  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ መአራር ኮሚሽን መረጃ መሰረት በድባጤ ወረዳ ጋሌሳ ቀበሌን ጨምሮ በሶስት ቀበሌዎች ላይ ከዚህ ቀደም የተፈናቀሉ ከ40ሺ በላይ ዜጎች ተጠልሎ ይገኛሉ፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ