1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሣዑዲ ዓረቢያ እንደ «ግሪን ካርድ» አይነት ፈቃድ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 6 2011

ሣዑዲ ዓረቢያ እንደ ዩናይድትድ ስቴትስ «ግሪን ካርድ» አይነት የመኖሪያ ፈቃድ ለውጭ ሃገራት ሕጋዊ ነዋሪዎች ለመስጠት እየተዘጋጀች ነው። «ጎልደን ካርድ» የተሰኘው የሣዑዲ የመኖሪያ ፈቃድ ረቂቅ ሕግ በሀገሪቱ ሹራ ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቊ ይፋ የኾነው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ነበር።

https://p.dw.com/p/3IUU2
Saudi-Arabien Riad
ምስል picture-alliance/NurPhoto/N. Economou

«ግሪን ካርድ» መሳይ ፈቃዱ ኢትዮጵያውያንን ይጠቅም ይኾን?

 የውጭ ሃገራት ነዋሪዎችን እንደሚመለከተው አዲሱ የሣዑዲ ዓረቢያ የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ሕግ ከኾነ፦ የውጭ ሃገራት ሕጋዊ ነዋሪዎች ከዚህ ሕግ ተጠቃሚ ለመኾን የትምህርት፤ የሥልጠና እንዲሁም የገቢያቸው መጠን ትኩረት ውስጥ እንደሚገባ «አራብ ኒውስ» ዘግቧል። አዲሱ የመኖሪያ ፈቃድ ሕግ የውጭ ሃገራት ነዋሪዎች በሣዑዲ ዓረቢያ ባሕል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማበረታታት ዓላማው ነው ተብሏል። የሌሎች ሃገራት ባሕልም ሣዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖረው እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጧል።

ነቢዩ ሲራክ   
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ