1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

“በረከትና ታደሰ ከማንም በላይ ያገለገሉ የመስዋዕት በጎች ናቸው፣ ይህ አይገባቸውም ነበር”

ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2012

የአቶ በረከት ባለቤት በበኩላቸው እነበረከት ምንጊዜም አሸናፊዎች ናቸው ብለዋል፡፡አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ከሳ ካለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በኋላ ደግሞ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ሲከራከሩ ቆይተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3bxIL
Äthiopien Konferenz in Mekelle Bereket Simon
ምስል DW/M. Haileselassie

የአማራ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአነ አቶ በረከት ስምዖን ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ

ፍርድ ቤቱ ሁለቱ የቀድሞዎቹ የኢህአዴግና የብአዴን ከፍተኛ ኃላፊዎች ላይ ቅጣቱን ያሳለፈው በስልጣን በነበሩበት ወቅት ሥራን በማይመች ሁኔታ መርተዋል በሚል ነው፡፡
የአቶ በረከት ባለቤት በበኩላቸው እነበረከት ምንጊዜም አሸናፊዎች ናቸው ብለዋል፡፡አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ከሳ ካለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በኋላ ደግሞ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ሲከራከሩ ቆይተዋል፡፡የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁለቱ የቀድሞዎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናትን የሙስና ጉዳይ ሲያከራክር የቆየ ቢሆንም ባለፈው ሰኞ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን ግለሰቦቹ የተከሰሱበት የሙስና አንቀፅ በወንጀል ህግ የሚታይ መሆኑን በማሳወቅ፣ አቶ በረከት ስምዖን በሁለት፣ አቶ ታደሰ ካሳ ደግሞ በሶስት ክሶች ሥራን በማያመች መንገድ መርተዋል በሚል ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ዛሬ የዋለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ በረከት ስምዖንን በ6 ዓመት ፅኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር፣ አቶ ታደሰ ካሳን ደግሞ በ8 ዓመት ፅኑ እስራትና በ15 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወሰኗል፡፡ፍርዱን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡን የአቶ በረከት ስምዖን ባለቤት ወ/ሮ አሲ ፈንቴ አንዳሉት  “በረከትና ታደሰ ከማንም በላይ ያገለገሉ የመስዋዕት በጎች ናቸው፣ ይህ አይገባቸውም ነበር” ብለዋል፡፡ይህንን እድል ያላገኙ ሰዎች አሉ ያሉት ወ/ሮ አሲ ወደ ሌላ ትግል መንገድ እንደተከፈተ እንደሚቆጥሩት አስረድተዋ ል ”እንኮራባቸዋለን እንጂ አናፍርባቸውም” ነው ያሉት፡፡፡ምናልባት የቀድሞ ባልደረቦቻቸው በፍርዱ እየተቀባበሉ ሊያወሩት ይችሉ ይሆናል እንጂ ግለሰቦቹ ንፁህ ናቸው  ሲሉም አስረድተዋል፡፡የእነ አቶ በረከት ጠበቃ ወ/ሮ ህይወት ሊላይ ሂደቱን በይግባኝ እንደሚቀጥሉበት ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ