1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሩስያ የተሰራዉ ጀበና

እሑድ፣ ታኅሣሥ 9 2009

አዲስ አበባ ከተማ ፍቅር የተያዘችዉ ሩስያዊቷ ወጣት ማርያ ከኢትዮጵያ ወደ ሃገርዋ ይዛ የተመለሰቻቸዉን የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና እቃዎችን በጥቅሉ ስትገልፀዉ „ትንሽ ኢትዮጵያን ይዤ ነዉ ወደ ሃገሬ የተመለስኩት“ ስትል ነዉ። እሷ ጋ ቡናን ሊጠጣ የሚመጣዉ ሰዉ በመብዛቱም ተለቅ ያለ ጀበናዉን ለምን አላሰራም ስትል አሰበች፤ ሞከረች፤ ተሳካላትም።

https://p.dw.com/p/2UTUC
Addis Kaffe in St. Petersburg äthiopischer Kaffe
ወ/ት ኤደን አለሙምስል Marina Korniyeva

አዲስ ካፌ

«የኢትዮጵያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባን ከጎበኘሁ በኋላ ነዉ። አዲስ አበባ ላይ ቡና ከጠጣሁ በኋላ የቡናዉን ጣዕም እጅግ ወደድኩት ፤ ወደ ሩስያ ተመልሼ የቡናዉን ዝግጅት በደንብ ከተማርኩ በኋላ፤ ትንሽ ቡና ቤት ለመክፈት በቃሁ። አብዛኞች በጣም ይወዱትላ።  እዚህ የምንጠጣዉን አይነት በየቀኑ የሚገኝ አይነት ቡና አይደለም፤ ወደር የሚገኝለት አይደለም»   

የ 27 ዓመትዋ ሩስያዊት የሳንት ፒተርስበር ከተማ ነዋሪና «የአዲስ ካፊ » ባለቤት ማሪያ ኮርኔይቫን ነበር ያደመጥነዉ። ማርያ ሸገርን ጎብኝታ ከተመለሰች ወዲህ በቡናዉ በእጣኑ  በቡና ቁርስ በፈንዲሻዉ በቂጣዉ ፤ በአንባሻዉ በአነባበሮዉ ፤ በጨጨብሳዉ ፤በ ቅንጬዉ በገንፎዉ፤ በእንግፍልፍሉ ሁሉ ብች ሁሉን ብንዘረዝር ማስጎብኘት እንዳይሆንብኝ በማሰብ ብዬ እዚህ ላይ ላቁም እንጂ በብዙ ነገር ተማርካ ነዉ ከኢትዮጵያ የተመለሰችዉ ። ማርያ በኢትዮጵያ በቡና ባህሉ ፍቅር  ተነድፋ ጀበና ፤ ረከቦት የጣን ማጤሻ የቡና ሙቀጫ ሳይቀራት ነዉ ይዛ ወደ ሩስያዋ ሳንት ፒተርስበርግ የተመለሰችዉ። ዘነዘናን ግን ደሞ ከሞላ ብረት ብላ ዘነዘናን እዚሁ ሩስያ ላይ ከጉማጅ ብረት ማሰራትዋንም ሰምተናል። የእለቱ መዝናኛ ዝግጅታችን የሩስያ ዉብ ከተማ በሆነችዉ በሳንት ፒተርስበርግ ዉስጥ ወደሚገኘዉ ወደ አዲስ ቡናቤት ይወስደናል።   

አዲስ አበባ ከተማ ፍቅር የተያዘችዉ ሩስያዉትዋ ወጣት ማርያ ከኢትዮጵያ ወደ ሃገርዋ ይዛ የተመለሰቻቸዉን የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና እቃዎችን በጥቅሉ ስትገልፀዉ „ትንሽ ኢትዮጵያን ይዤ ነዉ ወደ ሃገሪ የተመለስኩት“ ስትል ነዉ። ማርያ ኮርኔይቫ ፈንድሻ የሚቀርብበትን እጣን የሚጤስበትን ጉዝጓዝ ያለዉን በተለምዶ በደንቆሮ ሲኒ የሚቀርበዉን የኢትዮጵያ ባህላዊ ቡናን ሊጠጣ የሚመጣዉ ሰዉ በመብዛቱ ፤ ጀበናዉን ለምን አላሰራም ስትል አሰበች ፤ ሞከረችም ተሳካላትም።

«በእዉነቱ  መጀመርያ ከኢትዮጵያ ስመለስ ጀበናም ይዤ ነበር የተመለስኩት። ለኢትዮጵያ የቡና አፈላልባህል የሚስፈልገዉን ሁሉ ነገሮች ሁሉ ነዉ ያመጣሁት። ከዝያ ነዉ ጀበናንዉን እዚህ በእጅ ጥበበኞች ያሰራሁት፤ ግን ጀበናዉን አስመስሎ ለመስራት ቀላል አልነበረም አሁን ግን እዚህ በደንብ መስራት ይችላሉ።» 

ሩስያዉያኑ የተፈላዉን ቡና አበሻ ቀሚስ በለበሰች ሴት ሲካደሙ በፒተርስበር የከፍተኛ ትምህርቱን አጠናቆ እዝያዉ መኖር ሲኖር ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ያስቆጠረዉ አቶ ጌቱ ታደሰ ደግሞ ለቡናዉ ታዳሚዎች የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ያሳያል የአፈላሉን ስርዓት ያስረዳል፤  በጆሮ ያንቆረቁራል።   

ለሁለት ሳምንት ኢትዮጵያ ሄዳ የኢትዮጵያን ባህላዊ የቡና አፈላል ይዛ የተመለሰችዉ ኢትዮጵያዊት ዘነዘናዉን የቡና ዘነዘናዉን ከላዳ መኪና ብረት እንዴት አስቆርጣ እንዳሰራች አቶ ጌቱ ታደሰ ገልጾልናል።  

Addis Kaffe in St. Petersburg äthiopischer Kaffe
በሩስያ ከቀይ ሸክላ የተሰራዉ ጀበናምስል Marina Korniyeva

ወ/ት ኤደን አለሙ በሳንት ፒተርስበርግ አንድዬ ኢትዮጵያዊት መሆንዋ ይነገርላታል።  በሩስያ የሁለተኛ ዲግሪዋን ለመማመር ፒተርስበርግ ከገባች ሁለት ዓመት ሆንዋታል።

ማርያ ጋ ማለት አዲስ ካፊ  ባህላዊዉን የኢትዮጵያን ቀሚስ ለብሳ አሸንክታብዋን አጥልቃ ቡናዉን ስትካድም ሩስያዉያኑ በጣም እንደሚማረኩ ነግራናለች።  

በሩስያዋ ሳንት ፒተርስበርግ ከተማ አንድ የኢትዮጵያ ባህላዊ ቡና መጠጫ ቤት ቢኖርም ወ/ት ኤደን ባህላዊ ምግብን ለማቅረብ አነስ ያለች ሆቴል ለመክፈት እቅድ  አላት። አቶ ጌቱ ታደሰ በበኩላቸዉ በከተማዋ በግምት ወደ ሠላሳ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን ቤተሰብ መስርተዉ እንደሚኖሩ ነግሮናል።

የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ማፍያ «ጀበና» ከኢትዮጵያ ዉጭ ሲሰራ የሩስያዉ የመጀመርያዉ ሳይሆን ይቀራል ትላላችሁ? ግን ማርያ ጀበናዉ ተሰርቶ ከተሰጣት በኋላ አሟሽታዉ ይሆን ብቻ ጀበናዉ ጣዕም ያለዉ ቡናን እያፈላ ያዉ 60 የዩኤስ አሜሪካ ዶላር ማለትም ወደ 3600 የሩስያ መገበያያ ገንዘብ «ሩብል» እያስገባ ነዉ። አድማጮች ወቅታዊዉን የሩስያ በረዶና ብርዱን ተወት አድርገን በሩስያዋ ሳንክት ፒተርስበርግ ከተማ የኢትዮጵያን ባህላዊ የቡና መስተንግዶ የቃኘንበትን ሙሉ መሰናዶ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ