1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 17 2008

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ልክ የዛሬ ዓመት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግጭትና ጦርነትን ሸሽተዉ በረሃና ባህርን አቋርጠዉ በቀዝቃዛዉ የክረምት ወራት በግሪክ በባልካንና ሃንጋሪ ድንበር ላይ የተከማቹትን ስደተኞች ልቀቁዋቸዉ ወደ ጀርመን ይምጡ፤ ችግሩን በጋራ እንወጣዋለን ሲሉ ጥሪ ማሰማታቸዉ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/1JnhA
Angela Merkel Bundespressekonferenz
ምስል Reuters/H.Hanschke

[No title]


ይህ የሜርክልን የማይረሳ ጥሪ ዉሳኔና ዓለም ላይ የጀርመንን ገጽታ ቀይሮታል። አብዛኞች በዚህ ርምጃ ተገርመዋል፤ ተደንቀዋል። በሌላ በኩል ይህ ጥሪያቸዉ በመራሂተ መንግሥትዋ ላይ ተችዎችን አስነስቶባቸዋል። ሜርክል ስደተኞችን ተቀበሉ አስተናግዱ ብቻም ሳይሆን አንድ ላይ ሆነን ችግሩን እንወጣዋለን፤ በአንድ ላይም እንፈታዋለን ሲሉ ነዋሪዉን አበረታተዉም ነበር። ይህ በሰብዓዊነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የሜርክል ርምጃ የ 21ኛዉ ክፍለ ዘመን ክስተት ነዉ። እንድያም ሆኖ አሁን ከአንድ ዓመት በኋላ በተከተለዉ ችግር አብረን እንወጣዋለን የሚለዉ የሜርክል ጥሪ ጥያቄ ዉስጥ የገባ ይመስላል። በርግጥ እንወጣዉ ይሆን በሚል ርዕስ የዶቼ ቬለዉ አንድርያስ ቤከር የዘገበዉን የበርሊኑ ወኪላችን ተርጉሞ ልኮልናል።

አንድርያስ ቤከር / ይልማ ኃይለሚካኤል


አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ