1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሰብዓዊ መብት ላይ በዶይቸ ቬለ የተካሄደው ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 14 2003

የዶይቸ ቬለ «የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኸን መድረክ» ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። ከመላው አለም የመጡ ጋዜጠኞችና በተለያዩ ሙያ የተሰማሩ ግለሰቦች በልዩ ልዩ ርዕሶች ላይ እየተወያዩ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/RUxV
አቶ ኦባንግ ሜቶምስል Metho Obang

ሰብዓዎዊ መብት አንዱ የውይይት ርዕስ ነበር። ውይይቱ ላይ ንግግር ካደረጉት ውስጥ -አቶ ኦባንግ ሜቶ ይገኙበታል። የውይይታቸው ትኩረት ድጋፍና እርዳታ ስለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ነው። «ገዢው የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡን በጎሳ ከፋፉሏል፤ ይህ ሲሆን የአካባቢ ህዝቦችም በውሳኔ አሰጣጥ ላይ አልተካተቱም። ችግር አለ። እኛ ማለት የምንፈልገው ለነዚህ ሰዎች የምንቆም መሆናችንን ነው፤ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሰብዓዊነት! ኢትዮጵያዊም እንሁን ጀርመን ወደዚች ምድር ስንመጣ ቋንቋም ሆነ ሀይማኖት አልነበረንም። ወደዚህ ዓለም የመጣነው እንደ ሰው ነው። ሑላችንም ነፃ እስካልሆንን ድረስ አንድም ሰው ነፃ ሊሆን አይችልም።» ፤«የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ» የተሰኘው ማህበር ዋና ዳሬክተር- አቶ ኦባንግ ሜቶ ከተናገሩት የተወሰደ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ