1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሳዉዲ የኢትዮጵያዉያኑ ችግርና የዛሬ ዉሎ

ሰኞ፣ ኅዳር 2 2006

ሳዉዲ አረብያ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸዉን እና በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጭ ሀገር ዜጎችን እያሳደደች ማሰር ከጀመረች ሳምንትን አስቆጥራለች። የኢትዮጵያ መንግስት በሳዉዲ የሚገኙ ዜጎቹን ወደ ሀገሩ ለመመለስ ማቀዱ ከተሰማ በኋላ ዛሬ፤

https://p.dw.com/p/1AFXU
Foreign workers displays his passport as he waits outside a labour office, after missing a deadline to correct his visa status, in Riyadh November 4, 2013. The streets of the Saudi capital Riyadh were unusually quiet on Monday as many expatriates stayed at home to avoid the start of a government crackdown on illegal foreign workers. REUTERS/Faisal Al Nasser (SAUDI ARABIA - Tags: POLITICS BUSINESS EMPLOYMENT SOCIETY IMMIGRATION)
ምስል Reuters/Faisal Al Nasser

ሳዉዲ አረብያ ዉስጥ ይህንኑ ሥራ መጀመሩን ከዝያዉ ከሳዉዲ ተሰምቶአል። ይሁንና በሳዉዲ አረብያ ሕጋዊ መኖርያ ፈቃድ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ከ 25 ሽ በላይ ስለሚገመት፤ ስራዉን አቀላጥፎ ለመስራትና ዜጎች እንዳይጉላሉ ተጨማሪ የሰዉ ኃይል አስፈላጊ እንደሆነ ተመልክቶአል። ከዚህ ሌላ በሳዉዲ አርብያ መኖርያ ፈቃድ የሌላቸዉና በጥበቃ ስር ተይዘዉ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ባሉበት ቦታ የምግብና የመጠጥ ዉሃ እጥረት መከሰቱ ተነግሮአል። በሳዉዲ ያለዉ ሁኔታ ዉሎዉን ምን ይመስላል? ጅዳ የሚገኘዉን ወኪላች ነብዪ ሲራክን በስልክ ጠይቄዉ ነበር።

ነብዩ ሲራክ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ