1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሳውዲ ዐረቢያ ግንባታ ሰራተኞች ደሕንነት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2008

በስዑድ አረብያ መካ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ የጣርያ ሥራ በመስራት ላይ እያሉ ጣርያዉ በመደርመሱ አንዲት ኢትዮጵያዊት ስትሞት 18 የግብፅ ዜጎች መቁሰላቸዉ ባለፈዉ ሰሞን ተዘግቦአል።

https://p.dw.com/p/1JsPl
Saudi Arabien Infrastrukturprojekt Schnellzug Medina Mekka
ምስል picture-alliance/dpa/C. Moya

[No title]


ይህ ከመሆኑ አንድ ቀን በፊት በተለያዩ ሁለት የግንባታ ቦታዎች ሁለት የፓኪስታን ዜጎች ሕይወታቸዉን አጥተዋል። ባለፈዉ ዓመት ሚያዝያ ላይ እንዲሁ 10 የፓኪስታን ዜጎች በግንባታ ላይ ህንፃ በመደርመሱ ሕይወታቸዉ አልፎአል። የዛሬ አመት አካባቢ በመካ በተከሰተ የግንባታ ክሬን ተገልብጦ ከ 107 በላይ ሠዎች ሕይወታቸዉ አልፎአል። ከተለያዩ የዓለም ሃገራት የመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰራተኞች በተለይ ደግሞ ከእስያና አፍሪቃ የመጡ የጉልበት ሠራተኞች በስዑድ አረብያ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተዉ ይገኛሉ። እነዚህ ሕዝቦች በግንባታ ሥራ ላይ ምን ያህል ደሕንነታቸዉና ዋስትናቸዉ የተጠበቀ ነዉ። ወደ ቦን ራድዮ ጣብያችን ብቅ ያለዉ የስዑድ አረብያዉ ዘጋብያችን ስለሺ ሽብሩ ዘገባ አዘጋጅቶአል።

ስለሺ ሽብሩ


አዜብ ታደሰ