1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሳዑዲ የሪትስ ካርልቶን ቅምጥል ሆቴል እስረኞች ይዞታ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 20 2010

በሳዑዲ ዓረቢያ ሪትስ ካርልቶን ቅምጥል ሆቴል በቁጥጥር ስር ከሚገኙ ባለሐብቶች የተወሰኑት የመለቀቃቸው ዜና ይሰማል። በዛው መጠን ደግሞ ታሳሪዎች ላይ በደል ይፈጸማል የሚል ዘገባም ይደመጣል። የእስረኞቹ ወቅታዊ ኹኔታ ምን ይመስላል?

https://p.dw.com/p/2q74u
Ritz-Carlton in Saudi Arabien
ምስል picture-alliance/augenklick/firo Sportphoto/El-Saqqa

በሣዑዲ ቅምጥል ሆቴል ታሳሪዎች ወቅታዊ ኹኔታ

 የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በታሳሪዎቹ ላይ የሚያከናውነው ምርመራ እጅግ ሚሥጥራዊ ቢኾንም አንዳንድ ሾልከው የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አንዱ ሜጀር ጄነራል  ዓሊ አልቃታህኒ በደረሰባቸው የምርመራ ቁም ስቅል ሕይወታቸው መጥፋቱን እና ቤተሰቦቻቸውም የእስረኛውን አስክሬን ለመለየት እጅግ ተቸግረው እንደነበር ተገልጧል። ከእስረኞቹ መካከል ኢትዮጵያዊ ውስጥ በርካታ ኩባንያ ያላቸዉ ሼህ መሐመድ አላሙዲንም ይገኙበታል። የእስረኞቹ ወቅታዊ ኹኔታ ምን ይመስላል? ስቱዲዮ ከመግባቴ ቀደም ብሎ የሪያዱ ወኪላችን ስለሺ ሽብሩን በስልክ አነጋግሬው ነበር። ስለሺ ተለቀቁ ስለተባሉት እስረኞች በመግለጥ ይንደረደራል። 

ስለሺ ሽብሩ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ