1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

በሳዑዲ  የደሞዝ ቅነሳ ተጽዕኖ

ሐሙስ፣ ኅዳር 15 2009

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በጠቅላላው የመንግሥት ሠራተኞች ላይ የወሰነዉ የደሞዝ ቅነሳ በሀገሪቱ የንግድ መቀዛቀዝ ፤ በአብዛኛው የውጭ ሀገር ቅጥር ሠራተኞች ላይ ደግሞ ሥራን የማጣት ስጋት አሳድሯል፡፡

https://p.dw.com/p/2TBhY
Mazedonien Geld Denar
ምስል DW/E. Milosevska Fidanoska

Ber Riyadh (Impact of oil price decline in Saudi ) - MP3-Stereo

 

 ከያዝነው ወር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የደሞዝ ቅነሳ የሹራ ወይንም የሳዑዲ የበላይ ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ለመላው የመንግሥት ሠራተኞች በየደረጃው ይሰጥ የነበረውን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ፤ የማንኛውንም የአበል ክፍያ እንዲሁም የትራንስፖርት እና የቤት ኪራይ ክፍያን ሙሉ በሙሉ ከማንሳቱም በላይ ወርሀዊ ደሞዝን እስከ 20 በመቶ ቀንሷል፡፡ የሳዑዲ መንግስት ለዚህ የሰጠዉ ምክንያት ደግሞ የነዳጅ ዋጋ መቀነስ የፈ ሳቢያ በሀገሪቱ የተከሰተውን የባጀት ክፍተት ለመሙላትና ዜጎቹም የቁጠባ ኑሮ እንዲለምዱ የሚል ይገኝበታል፡፡ ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ተጨማሪ ዘገባ አለው ፡፡

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ