1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶማልያ የሰላም ጥረት እና የገንዘብ ሃይል እጦት

ረቡዕ፣ ጥር 16 1999

ሶማልያን ለመረጋጋት በሚደረገዉ ጥረት ስንኩል እድል አጋጥሞታል ሲሉ የአፍሪቃዉ ህብረት ምክትል ሊቀ-መንበር Patrick Mazimhaka በዛሪዉ እለት ለፋይናንሽያል ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/E0hP
በሶማልያ አንድ መንደር
በሶማልያ አንድ መንደርምስል AP

የሶማልያን የሽግግር መንግስት ለማገዝ እና በሶማልያ ሰላም ለማስፈን ይዘምታል ለተባለዉ 8000 ያህል የአፍሪቃዉ ህብረት ጦር ሰራዊትን ለመርዳት አፍሪቃ ካልሆኑ አገሮች ግልጽ የሆነ አሳቢነት እና ሃላፊነት አይታይም ብለዋል። በገንዘብ እጥረት የአፍሪቃዉ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር ሰላምን ለማንገስ ያለዉ አቅም ይመነምናል ነዉ። በሌላ በኩል የአዉሮፓዉ ህብረት ለሶማልያ ሰላም ጥረት 15 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት አቅዶአል። አዜብ ታደሰ ዝርዝር ዘገባ አላት።


የአፍሪቃዉ ህብረት ምክትል ሊቀመንበር Patrick Mazimhaka በአሁኑ ወቅት በሶማልያ ይላሉ ዛሪ ጠዋት ለFinanichial Times ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ በአሁኑ ወቅት በሶማልያ ፀጥታን ለማስፈን መሰራታዊዉ ነገር በተቻለ አቅም እና በተቻለ ፍጥነት የሰላም አስካባሪ ጦር ሃይላትን በአገሪቱ ማሰማራት ነዉ። የአፍሪቃ አገሮች የሚመለከቱት የተረጋጋ አካባቢን እና ቦታን ብቻ ነዉ፣ ይህን የተረጋጋ አካባቢን ለመፍጠር ግን በቅድምያ የሰላም አስከባሪ ሃይል መላክ ያስፈልጋል። ባለፈዉ ሳምንት አርብ የአፍሪቃ ህብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ የአፍሪቃ አገራት አምባሳደሮች ታካፋይ የሆኑበት ስብሰባ 8000 ያህል የአፍሪቃዉ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር ወደ ሶማልያ ለማሰማራት ነዉ። በትናንትናዉ እለትም የኢትዮጽያ ጦር ወደ አገሩ መመለሱን ጀምሮአል። ነገር ግን እስከ አሁን በሶማልያ የአፍሪቃዉ ጦር ሰላም ለማስከበር እንዲገባ መወሰኑ እንጂ ዉሳኔዉ ገቢራዊ አልሆነም። በሶማልያ የአፍሪቃዉን ህብረት ጦር ለማሰማራት እስካሁን ዉሳኔዉ ተፈጻሚነት ያላገኘዉ የጦር ሃይሉን የማሰባሰቡ ችግር ወይንስ የገንዘብ ችግር የInternational Grupps ማለት አለም አቀፉ የዉጥረት ጉዳይ አማካሪ ማት ብራይደን ችግሩ የገንዘብ ብቻ አይደለም ባይ ናቸዉ
«እንደኔ ግምት የአፍሪቃዉ ህብረት በዉጥረት ላይ ነዉ የቆየዉ። የዳርፉርን ጉዳይ እንደምሳሌ ልንጠቅስ እንችላለን። በሶማልያ በቅርቡ የሰላም አስከባሪ እናያለን ብዩ አስባለሁ ግን 8000 ሺህ ያህል ጦር የመሰማራቱ ጉዳይ በርግጥም አጠራጣሪ ነዉ። እዚህ ላይ ዋናዉ ቁም ነገር እና ለሰላም መስፈኑ ጥረት ዋነኛዉ ቁልፍ የጦር ሰራዊቱ ቁጥር መብዛት፣ ማነስ ወይም ደግሞ የገንዘብ አቅም አይደለም»
እንደ ብራይደን ሃሳብ፣ በሶማልያ የሚዘምተዉ የጦር ሰራዊት የመጀመርያ አላማ ምንድን ነዉ ? የሚለዉ ነዉ። አላማዉ የኢትዮጽያን የጦር ሰራዊት መተካት እና በአገሪቷ ገና በስፋት ተቀባይነትና ታዋቂነት ለሌለዉ መንግስት ድጋፍ ከሆነ፣ እንደኔ ግምት በርካታ የአፍሪቃ አገር መንግስታት የጦር ሃይሎቻቸዉን መላክን አይሹም! ምናልባትም ለሰላም ማስከበር ተልኮ ያሰማሩት ጦር ትልቅ ትግል እና ፍልምያ ዉስጥ ሊወድቅ ይችላል በሚል ስጋት። ስለዚህም እዚህ ላይ የጠበቅነዉን ያህል የሰላም አስከባሪ ሰራዊት በሶማልያ ልናገኝ ወይም ልናሰማራ የምንችል አይመስለኝም። በሁለተኛ ደረጃ ይላሉ ብራይደን፣ በዚህ መልኩ የሰላም አስከባሪ ጦር በሶማልያ ተልኮዉ ስኬታማ አይሆንም! ምክንያቱም ጦሩ የተደራጀ ሆኖ፣ በአገሪቷ ህገ-መንግስት ተቋቁሞ ለምርጫ እንዲዘጋጅ፣ እንዲሁም በአገሪቷ የጦር ሃይል ተቋቁሞ ተጻራሪ ወገኖች በአንድ ጠረቤዛ ወይይት የሚቀርቡበት መድረክ መፍጠር መጫሉ ነዉ። በብሄራዊ ጥሪ ከሽግግር መንግስቱ እና ከሸርያ ፍርድቤቶች ህብረት እንዲሁም ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ለድርድር መድረክ ዝግጅት ካለ፣ ሰላም የማስፈኑ ጉዳይ ሲኬታማነት ይኖረዋል። በዚህ ረገድ የአፍሪቃ አገሮች ገንዘብ እና የሰላም አስከባሪ ሃይልን ማሰባሰቡን በሙሉ ልብ ሊቀበሉት ይችላሉ።
የአዉሮፓ ህብረት በሶማልያ የሰላም መስፈን 15 ሚሊዮን ዩሮ መስጠት አቅዶአል። ይሁንና የህብረቱ ቃል አቀባይ አማዱ አልታፋጅ እንደሚሉት ገንዘቡን ለመስጠት በሶማልያ የሽግግር መንግስት እና በተቀናቃኝ ሃይላት መካከል ፖለቲካዊ ድርድር መጀመሩ አስፈላጊ ነዉ።

«በሶማልያ ስለሚደረገዉ የሰላም ጥረት 15 ሚሊዪን ዩሮ አግኝተናል። ዩናይትድ ስቴትስም ለዚሁ ጥረት ትብብሯን ለማድረግ ዝግጁ ናት። ሁሉም ለዚህ ሰላም ጥረት የገንዘብ እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ ነዉ። ነገር ግን ሰላም ማስፈኑ የሚደረገዉ ጥረት አንድ ነገር ሆኖ ሳለ በተቀናቃኝ ሃይላት እና በሶማልያ የሽግግር መንግስት መካከል ፖለቲካዊ ድርድር ካልተካሄደ ችግር ነዉ። በሶማልያ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ ዉጥረት እና ብስጩነት ነዉ የሚታየዉ»

አልታፋጅ ድርድሩ ካልተካሄደ የሰላም ለማሰፈን የሚደረገዉ ጥረት በሰላማዊ መንገድ ሳይሆን የሃይል ጥረት ይሆናል። ታድያ ይህ ለሰላም እና መረጋጋት መሰረት አስፈላጊ የሆነዉን መንገድ መያዙን ትቶ አቅጣቻዉን ይስታል ነዉ።