1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶማልያ፣ የአጋቾች ዛቻ

ሰኞ፣ ግንቦት 6 1999

በሶማልያ ራስ ገዝ በሆነችዉ ሰሜናዊ ፑንትላንድ ግዛት ታጣቂዎች ያፈንዋቸዉን ሁለት የግብረሰናይ ድርጅት ሰራተኞች እንደሚገድሉ ዛቱ

https://p.dw.com/p/E0YM

የጸጥታ ሃይላት፣ ታጣቂዎቹ ያገታቸዉን ሁለት የግብረሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ለማስለቀቅ ቢሞክሩ፣ እንገላለን ሲሉ ለአካባቢ ሽማግሌዎች አስታዉቀዋል። በሶማልያ ስለታገቱት የድርጅቱ ሰራተኞች በጀርመን ቦን የሚገኘዉ CARE International ቢሮ ቅርንጫፍ ቃል አቀባይን አዜብ ታደሰ አነጋግራለች

CARE International የተሰኘዉ የግብረሰናይ ድርጅት ባልደረቦች በሶማልያ ፑንት ላንድ ግዛት ዉስጥ በታጣቂዎች መታገታቸዉን የተሰማዉ ባለፈዉ ሳምንት ዉስጥ ነበር። በሰሜናዊ ፑንትላንድ የታገቱት አንድ ብሪታንያዊ እና አንድ የኬንያ ተወላጅ መሆናቸዉ ታዉቋል። ባለፈዉ ሳምንት አርብ CARE International የግብረሰናይ ድርጅት ታጋቾቹ በደህና ሁኔታ እንደሚገኙ ገልጾ ነበር። የፑት ላን አካባቢ አዛዉንት እንዳስታወቁት የጸጥታ አስከባሪ ሃይላት ታጋቾቹን ለማስፈታት ቢሞክሩ እንገላለን ሲሉ ዝተዋል ሲል ስም ጠቅሶ የፈረንሳይ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሪስ ገልጾአል።
በጀርመን ቦን ከተማ የሚገኘዉ CARE International የግብራሰናይ ድርጅት ቅርንጫፍ ቢሮ ቃል አቀባይ Thomas Schwarz እንደገለጹት በሶማልያ የዚህ ድርጅት ሰራተኛ የሆነ ጀርመናዊ ተወላጅ የለም ቢሆንም ቅሉ የድርጅቱ ባልደረቦች በመታገታቸዉ በጣም ሃሳብ ላይ ነን። አሁን ልናረጋግጥላችሁ የምንችለዉ ወይም መግለጽ ያለብን ነገር ሁለት የስራ ባልደረቦቻችን መታገታቸዉን ነዉ
«CARE International የተሰኘዉ የግብረሰናይ ድርጅት አማካሪዎች፣ ማለት ሁለት ወንድ የድርጅቱ ሰራተኞች፣ አንድ ከብሪታንያዊ እና አንድ የኬንያ ተወላጅ መጥፋታቸዉን ነዉ ልናረጋግጥ የምንችለዉ። በአሁኑ ወቅት ከአካባቢዉ አረጋዉያን እና ታዋቂ ሰዎች ጋር ሆነን ሁኔታዉን በማጣራት ላይ እና ችግሩን ባፋጣኝ መፍትሄ እንዲገኝ እየጣርን ነዉ»
የፈረንሳይ ዜና ወኪል ይፋ እንዳደረገዉ እስካሁንም የአካባቢዉ የጸጥታ ሃይላት ለሁኔታዉ መፍትሄ ለማምጣት አለመሞከራቸዉ ተረጋግጦአል። እንደ አካባቢዉ ምስክሮች አገላለጽ የጸጥታ ሃይላቱ የአካባቢዉ ሽማግሌዎች መፍትሄዉን እንዲያገኙ እድል ሰጥተዋቸዉል ተብሎአል። ባለፈዉ ሳምንት የጠፉት CARE የተሰነዉ አለማቀፍ የግብረሰናይ ድርጅት ሰራተኞች በከፊል ራስ ገዝ በሆነችዋ በፑንት ላንድ እና በሰሜናዊ ሶማልያ የባህር ወደብ፣ ለግንባታ ስራ፣ ቅየሳ ላይ እንደ ነበሩ ተገልጾአል። አጋቾቹ ጥያቅያቸዉ ምንድን ነዉ ይላሉ ለሚለዉ Thomas Schwarz
«ምን እንደሚፈልጉ ምንም መናገር አንችልም! አንሻም! በርግጥ ከአጋቾቹ ጋር በአካባቢዉ አዛዉንቶች አማካኝነት ድርድር ላይ ነን ፣ ንግግሮችን እየተለዋወጥን ነዉ። ችግሩ በጸጥታ እና በወዳጅነት ለመፍታት እየሞከርን ነዉ። በርግጥ መፍትሄ እንዳገኘን ለመገናኛ ብዙሃን ማሳወቃችን አይቀርም»
CARE International ሰራተኞቹ ለምን እንደታገቱበት የገለጸዉ ነገር ባይኖርም፣ ባለፈዉ ሳምንት በህግወጥ መንገድ አሳ ሲያጠምዱ በፑንት ላንድ ባለስልጣናት የተያዙትን ጀልባዎች ለማስለቀቅ ነዉ ሲሉ የባህር ወደብ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ሁለቱ CARE International የግብረሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ከደቡባዊ ምስራቅ ፑንትላንድ 120 km አርቃ ከምትገኘዉ ዋነኛ ከተማ Bossaso ዉስጥ መጠለፋቸዉም ታዉቋል።