1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት ጉዳይ ችሎት

ረቡዕ፣ ጥር 24 2009

ጠበቆቹ ዛሬ ለፉደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ነኛ ወንጀል ችሎት በጽሁፍ ባቀረቡት ምላሽ ዓለም አቀፍ ህጎችን ፣ የኢትዮጵያን ህገ መንግሥት እና ሌሎች ተዛማጅ ህጎችን በመጥቀስ ችሎቱ በግልጽ መታየት አለበት ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/2WnZj
Symbolbild Hammer Gericht
ምስል Fotolia/Gina Sanders

M M T/ Beri AA (Court hearing) - MP3-Stereo

በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ወቅት ለደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተከሰሱት 38 ተከሳሾች ጉዳይ በዝግ ችሎት ይታይልኝ ብሎ አቃቤ ህግ ያቀረበው አቤቱታ ተቃውመው የተከሳሾቹ ጠበቀች መልስ ሰጡ ። ጠበቆቹ ዛሬ ለፉደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ነኛ ወንጀል ችሎት በጽሁፍ ባቀረቡት ምላሽ ዓለም አቀፍ ህጎችን ፣ የኢትዮጵያን ህገ መንግሥት እና ሌሎች ተዛማጅ ህጎችን በመጥቀስ ችሎቱ በግልጽ መታየት አለበት ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ