1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በበርሊኑ የፊልም መድረክ ሽልማት/የተ.መ.ድና ቋንቋ

እሑድ፣ የካቲት 14 2002

የጀርመን መዲና በርሊን የአለም የሲኒማ መድረክ ሆና ሰንብታለች። የካቲት አራት ቀን የስድሳኛ አመቱን ያከበረዉ የበርሊኑ የፊልም መድረክ በአመት አንድ ግዜ የአለም የፊልም አዋቂዎችና ተጫዋቾችን ማስተናገድ የጀመረዉ የበርሊኑ የፊልም ማዕከል ዛሪ ተጠናቆዋል።

https://p.dw.com/p/M7Hx
ቱርካዊዉ ተሸላሚ ስሚህ ካፕላንግሉምስል picture alliance / dpa

የፊልም ማዕከሉ ትናንት ምሽት የአመቱ ምርጥ ፊልም በማለት እዉቁን ወርቃማ የድብ ቅርጽ ሽልማት በቱርክ ቋንቋ /Bal / በአማረኛችን ማር ለተሰኘዉ የቱርክ ፊልም አበርክቶአል። ቱርክ ዘንድሮ በአለም የፊልም መድረክ ከፍተኛ ክብር ያለዉን የበርሊናለን ሽልማት ስታገኝ የትናንትናዉ ከ 46 አመት በኻላ ለመጀመርያ ግዜ መሆኑ ነዉ። ሌላዉ በጀርመን የባህል ድረ-ገጾች ላይ አበይት ሆነዉ ከሰፈሩ ባህል ነክ ጉዳዮች የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት UNESCO እዚህ በቦን ከተማ ያለዉ ቅርንጫፍ በአለማችን ዙርያ ሚነገሩ 6000 ያህል ቋንቋዎች መካከል ገሚሱ እንዳይጠፋ ያሰጋል ሲል ይገልጻል። በቦን ከተማ UNESCO ቢሮን በጉዳዩ ዙርያ ባለሞያ አግኝተን አነጋግረናል። በዛሪዉ መረሃ ግብራችን በሁለተኛነት የያዝነዉ ርእሳችን ነዉ ከጥንቅሩ ጋር አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ!

ዛሪ አስራ አንደኛ ቀኑ የተጠናቀቀቁ በጀርመን የበርሊኑ የፊልም መዕከል ስድሳኛ አመት ድግስ በፊልም ስራ ጥበብ ጥሩ ያላቸዉን ፊልሞች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ የፊልም ስራ አዋቂቆች እና ደራሲዎችን ሽልማት በመስጠት ተጠናቆዋል። በአለም ዙርያ ባሉ አገሮች የተሰሩ አራት መቶ ያህል ፊልሞችን አይቶ እና ገምግሞ ትናንትና ምሽት ሽልማቱን ለአሸናፊዎች አበርክቶአል

ከ46 አመታት በኻላ ቱርክ ምርጥ ፊልም ስራ ሽልማትን ከበርሊኑ የፊልም ማዕከል ስታገኝ የትናንት ምሽቱ ለመጀመርያ ግዜ ነዉ። በአማረኛችን ማር የተሰኘ መጠርያ ያለዉ የቱርኩ ፊልም አንድ ታዳጊ ህጻን በተራራ ደን በታጠረ ለምለም ገጠር ከተማ በጥሩ ሁኔታ ከአባቱ ጋር ሲኖር አባቱ በድንገት ሞቶ፣ አስደሳች እና ጥሩ ቀላል ህይወት የነበረዉ ኑሮ በአባቱ ትከሻ በመኖሩ ብቻ አለማወቁን ግን ከአባቱ ሞት በኻላ ህይወት ከባድ እንደሆነ እንደ ተገለጸለት የሚያሳይ ፊልም እንደሆነ ተገልጾአል። በበርሊናለዉ የፊልም መድረክ ለብዛኞቹ የፊልም ስራ አዋቂዎች እና ሃያስያን ተወዳጅ ፊልም እንደነበረም ተገልጾአል።
"The Ghostwriter" ለተሰኘዉ ጥሩ የፊልም ቅንብር በቁም እስር ስዊዘርላንድ የሚገኙት የፊልም ስራ አዋቂ፣ ደራሲ እና የፊልም ተዋናይ የፈረንሳይ እና የፖላንድ ዜግነትን የያዙት የ 67 አመቱ Roman Polański የበርሊናለዉን የብር ድብ ቅርጽ ሽልማት አግኝተዋል። Polański እ.አ 1977 አ.ም በአሜሪካን አገር የ 14 አመት ልጅ ደፍረሀል ተብለዉ ነዉ፣ ባለፈዉ አመት ስዊዘርላንድ አየር ጣብያ በድንገት የተያዙት። የፍርዱ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ለፍርድ ወደ አሜሪካ እንደሚዛወሩ ይጠበቃል።

Flash-Galerie Der Ghostwriter
የፊልም ስራ አዋቂዉ ሮማን ፖላንስኪምስል Kinowelt

ዘንድሮ ታድያ የበርሊኑ የፊልም ማዕከል መድረኩን ከእስያ አህጉር በቻይና የፊልም ስራ አዋቂ በተሰራ ነዉ የጀመረዉ። የፊልም መድረኩ የፊልም እያታዉን የሚያጠናቅቀዉ ከዝያዉ ከእስያ አህጉር በጃፓን በተሰራ ፊልም እንደሆነም ተጠቁሞአል። ባለፈዉ እሁድ ምሽት በፊልም ማዕከሉ በበርሊናለ ዋና መለያ የመግብያ ቀይ ምንጣፍ ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረዉ ከዝያዉ ከእስያ ከህንድ በእንግድነት የመጣዉን የቦሊዉዱን የፊልም አክተር Shah Ruka Khan ን ለማየት ነበር። በጀርመን በርካታ አድናቂዎችን ያፈራዉ የቦሊዉዱ አክተር በበርሊን ከፍተኛ መድረክ ላይ ሲገኝ ይህ ሁለተኛዉ ነዉ። ጀርመን ዉብ የሆኑ ወንዶችም ሴቶችም አሏት ግን ደግሞ ሴቶቹ ይበልጥ ዉቦች ናቸዉ፣ በማለት የጋዜጠኞችን ቀልብ የሳበዉ የቦሊዉዱ ኮከብ የፊልም ተዋናይ Shah Ruka Khan ሴቶቹን መዉደዱ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ፊልም ይዞ በጀርመኑ የፊልም ማዕከል እንደተገኘ፣ በሰጠዉ ቃለ ገልጾአል። «My Name is Khan » ይላል ስሜ ካን ይባል ይሰኛል በህንድ የፊልም ማዕከል በቦሊዉድ የተቀናበረዉ ፊልሙ። የጀርመን የህዝብ መገናኛዎች እንደዘገቡት ህዝብ የቦሊዉዱን ፊልም ለማየት የመግቢያዉን ትኬዝ ተሻምቶ ነዉ የገዛዉ። «My Name is Khan » የተሰኘዉ ፊልም በዩናይትድ ስቴትስ ኒዮርክ አሸባሪዎች ባደረሱት ጥቃት ሳብያ ከ9/11 በኻላ በእስልምና ሃይይማኖት ተከታዮች ላይ የሚታየዉን ፍርዳዊ ያልሆነ ነቀፊታና አመለካከትን ያንጸባርቃል። የቦሊዉዱ ኮከብ የሚል ስያሜ ያለዉ የህንዱ የፊልም ተዋናይ Shah Ruka Khan ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነዉ።
ሌላዉ Invictus የተሰኘዉ ፊልም የበርሊኑን የፊልም መድረክ ቀልብ ስቦ የሰነበተ ፊልም ነበር። እዉቁ ጥቁር አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይ Morgan Freeman የኔልሰን ማንዴላን ገጸ-ባህሪ ተላብሰዉ የሚጫወቱበት Invictus የተሰኘዉ ፊልም በአማረኛችን አይበገሪ እንደማለተን ነዉ፣ በአፓርታይድ ስርአት የምታወቀዋ በቀድሞዋ ደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ ተገርስሶ እንደ አዉሮጻዉያኑ 1995 አ.ም አገሪቷ የአለም የስፖርት ዉድድር የRugby ማለት የእጅ ኻስ ጨዋታን አዘጋጅታ የአለምን ህዝብ በእስፖርት መድረክ በማገናኘት በአዲሲትዋ ደቡብ አፍሪቃ የሰዉ ልጆችን እኩልነት በማንጸባረቅ የአገሪቷን ጥሩ ገጽታ የሚያሳይ ነዉ። የአሜሪካዊ ኮከብ የፊልም ተዋናይ Michail Gorbatschow ደቡብ አፍሪቃን ከአፓርታይድ ነጻ ያወጣት ኔልሰን ማንዴላን በመሆን ተመርጠዉ ይህንን ፊልም በመጫወታቸዉ እጅግ ኩራት እንደተሰማቸዉ ገልጸዋል። በነገራችን ላይ ይህ ፊልም በጀርመን ሲኒማ ቤቶች መታየት ከጀመረ ሰነባበተ

Cinema for Peace ሲኒማ ለሰላም በተሰኘዉ የበርሊናለ መረሃ ግብር ላይ በአለማችን ዙርያ ታዋቂ የተባሉ በርካታ ፖለቲከኞች እና የፊልም ተዋናዮች ተገኝተዋል። ባለፈዉ አመት በበርሊኑ የፊልም ማዕከል ባከበረዉ አመታዊ ቀኑ የሆሊ ዉዱ Leonardo DiCaprio ተገኝቶአል። Leonardo DiCaprio በተለይ ታይታኒክ በተሰኘዉ ፊልም በአለም የፊልም መድረክ ታዋቂነትን ያገኘ ነዉ። Leonardo DiCaprio ሴት አያቱ ጀርመናዊት እንደሆኑ በመግለጽ ለጀርመን ለየት ያለ ዝምድና እና ፍቅር እንዳለዉ በመግለጽ በጀርመንኛ ቋንቋ እየሞካከረ ሃሳቡን ለጋዜጠኖች ገልጿል። Cinema for Peace በተሰኘዉ ምሽት ላይ የሰላም ኖቤል ተሸላሚዉ ሩስያዊዉ Michail Gorbatschow ዋንኛዉ እንግዳ በመሆን ተገኝተዉ ነበር።።
በዘንድሮዉ የበርሊኑ የአለም የፊልም መድረክ "Kinshasa Symphony" የተሰኘ ጥናታዊ ፊልም በጀርመናዊዉ የፊልም ሰራተኛ Claus Wischmann ተቀናብሮ ቀርቦአል። ፊልሙ በኮንጎ ኪንሻሳ ከተቋቋመ 15 አመት ያስቆጠረዉ የክላሲካል ማለት የረቂቅ ሙዚቃ ቀማሪዎች ቡድን በተለይ የጀርመኑን የክላሲካል ሙዚቃ ጠቢብ Ludwig van Beethovenን የሙዚቃ ስራዎች ሲቀምሩ ያሳየል። የሙዚቃ ቡድኑ በርግጥ ከባድ የሆነዉን የሙዚቃ ቅንብር የሙዚቃ ድርሰቶች ይህ አይነቱ ባህል በሌለበት አካባቢ መሞከሩ በመደነቅ ይመስላል፣ ይህ ጥናታዊ ፊልምም የቀረበዉ። በበርሊናለ የቀረበዉ "Kinshasa Symphony" የተሰኘዉ ጥናታዊ ፊልም ሙዚቃ ቡድን በቂ ሙዚቃ መሳርያ የሌለዉ የሙዚቃ መሳርያዉ ብልሽት ሲገጥመዉ በተለዩ ዘዴዎች በመጠገን የBeethovenን የሙዚቃ ስራዎች ለመጫወት መሞከሩ ለየት ያለ መሆኑን በማንጸባረቅ የቀረበ አፍሪቃ ነክ ፊልም ነበር።

Symbolbild Unesco Logo und die arabische Welt
ምስል AP Graphics/DW
Flash-Galerie Oscar Nominierungen 2010
ማንዴላም ገጸ-ባህሪ ተላብሰዉ የሚጫወቱት የሆሊዉዱ ኮከብ ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማንምስል picture-alliance/dpa

የተ.መ.ድ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ታስቦ ዋላ

በያዝነዉ ሳምንት መገባደጃ ላይ ቦን የሚገኘዉ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ የባህል ተቋም UNESCO ቢሮ በአለማችን ህዝብ የሚገለግልባቸዉ ቋንቋዎች መካከል በየሁለት ሳምንቱ አንድ ቋንቋ እየጠፋ ነዉ ሲል ዘገባዉን አዉጥቶአል። ተቋሙ ይህንን ጥናቱን ይፋ ያደረገዉ ዛሪ የካቲት 14 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀኑን የትዉልድ ቋንቋ ቀን በማለት ታስቦ የሚዉልበትን ቀን በማስታከክ ነዉ። የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት UNESCO የዛሪ 10 በአለማችን ዙርያ የሚነገሩ ቋንቋዎች መካከል በርካቶች እየመነመኑ በመሄዳቸዉ የሁኔታዉን አሳሳቢነት በመገንዘብ ነዉ የካቲት 12 ን የትዉልድ ቋንቋ ቀን ብሎ ሰይሞ ህዝቦች የአፍ መፍቻ ቋንቋዎቻቸዉን እንዲጠብቁ በያመቱ ቀኑ በአለም ዙርያ እንዲታሰብ የሆነዉ።

እዚህ የራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት በቦን ከተማ የድርጅቱ ጽ/ቤት ቅርንጫፍ የዛሪዉን ቀን በማሰብ በያዝነዉ ሳምንት መገባደጃ ላይ ባወጣዉ ዘገባ በአለማችን ዙርያ ከሚነገሩ 6000 ቋንቋዎች መካከል ገሚሱ እንዳይጠፋ ያሰጋል ሲል ዘግቦአል። በማያያዝ በጀርመን ብቻ 13 ያህል ቋንቋዎች የሚናገራቸዉ ህዝብ በመመንመኑ ግልጋሎታቸዉ ጨርሶ መቀነሱንም አስታዉቋል። በአለማችን ዙርያ ህዝብ የሚገለግልባቸዉ ቋንቋዎች መመንመናቸዉ ዋንኛ ምክንያት ይላል ድርጅቱ በመጀመርያ ደረጃ ጦርነትና ግጭት ፣ ስደት እንዲሁም ቋንቋን ከቋንቋ መከለስ አጉል ባህል መሆኑን ያሳያል። በቦን ከተማ ባለዉ የድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት የአለም የባህል ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ክርስቲነ ማርታ ሜርክል
«ቋንቋ ሞተ ስንል ቋንቋዉን የሚናገረዉ ህዝብ ቁጥሩ ቀነሰ አልያም የሚናገረዉ ሰዉ የለም ማለት ነዉ። በአለማችን ዙርያ ከሚነገሩ 6000 ያህል ቋንቋዎች መካከል 200 ያህሉ በጽሁፍም መልክ ሆነ በቃል የሚናገረዉ ሰዉ የለም። ምናልባትም 1000 ያህል ህዝብ ይናገረዉ ይሆናል። አልያም ቋንቋዉ የአነጋገር ስልቱ ተለይቶ ቋንቋዉ መሰረቱን አጥቶአል»
በቦን ከተማ በሚገኘዉ የዩኒስኮ ቦሮ ቅርንጫፍ ጽ/ፈት ቤት የባህል ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ክርስቲነ ማርታ ሜርክል፣ የቋንቋ መሞት ዋንኛ ምክንያት ከጦርነት ከግጭት ሌላ፣ የምንናገረዉን ቋንቋ ለልጆቻችን ባለማስተማራችን፣ በጽሁፍ ወይም በሌላ ባህላችንን በሚገልጽ መልኩ ለልጅ ልጆቻችን ባለማስተላለፋችን እና ቋንቋን ከቋንቋ በመደባለቃችን ዋንኛ ምክንያት ነዉ ሲሉ ያስረዳሉ። ለምሳሌ በአለማችን ይላሉ «በአዉሮጻ ዉስጥ ጨርሶ የጠፋ ቋንቋ አለ። ይህ የሆነዉ ከሰላሳ አመት ግድም በፊት ነዉ። በአላስካ የበረዶ ላይ ነዋሪዎች ማለት የኤስኪሞዎች ቋንቋም እንዲሁ ጨርሶ ጠፍቶአል። በቱርክ ዉስጥም አንድ ጎሳ የሚናገረዉ ቋንቋ ጨርሶ ከጠፋ ሰላሳ አመት ሆኖታል»

ለምሳሌ በጀርመን ዉስጥ የሚነገረዉ የስርብ የስሎቭያን የቋንቋ ዝርያ ጠፍቶአል፣ በምስራቅ ጀርመን ያሉ ህዝቦች በጥንት ግዜ ይጠቀሙበት የነበረ ቋንቋ ነዉ። ሌላዉ በሰሜን ጀርመን ባሉ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ ህዞች ይናገሩት የነበረዉ የፍሪስሽ ታሪክ አዘለ የነበረ ቋንቋ በመጥፋት ላይ ነዉ። በባቫርያ ግዛት እንዲሁ እየጠፋ ያለ በግዛቱ ብቻ የሚነገር ቋንቋ ተጠቃሽ ነዉ»

እንደ ጀርመናዊትዋ አዋቂ ቋንቋን ጠብቆ ለማቆየት የጽሁፍ የትክክለኛ ትምህርት እና በተለይ በመገናኛ ብዙሃን ቋንቋዉን መጠቀም፣ ቋንቋዉ እንዲያድግ እና ተጠብቆ እንዲኖር ከፍተኛ ድጋፍን የሚሰጥ ዋንኛ ዘዴ ነዉ

አዜብ ታደሰ