1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በበርሊን የአለም የባህል መናኻርያ

Azeb Tadesseእሑድ፣ ሐምሌ 5 2001

በጀርመን ዋና ከተማ በበርሊን የአለም የባህል መናኻርያ በሚል ሊሰራ የታቀደዉ የአለም የባህል ሙዝየም ሊሰራ እቅድ ላይ ከወጣ ሃያ አመታት ሊያስቆጥር ቢሆንም ሙዚየሙ

https://p.dw.com/p/Ilw0
የሙዝየሙ ምስል በዕቅድምስል DW


ይገነባል አይገነባም ዉሳኔ ሳየገኝ አመታትን አስቆጥሮአል። የመሃል ከተማዋ የበርሊንን ክፍል የከበበዉ ሰዉ ሰራሹ የሽፕሪ ወንዝን ተንተርሶ ሊሰራ የታየቀደዉ Humboldt-Forum ተብሎ የተሰየመዉ ይህ ግዙፍ የአለም የባህል መናኻርያ የአለም ቅርሶች የሳይንስ ግኝቶች እንና ባህልን የሚያንጸባርቁ መጻህፍት የሚገኙበት ትልቅ ቤተ መጻህፍት እንደሚያጠቃልል ታዉቋል። ይህንኑ የአለም የባህል መናኻርያ ህንጻ እንዲሰራ ቀያሽ መሃንዲስን ለማግኘት በአለም አቀፍ ደረጃ በተደረገዉ ዉድድር ጣልያናዊዉ መሃንዲስ Franco Stella ማሸነፉ ባለፈዉ የአዉሮጻዉያኑ 2008 አ.ም መጸረሻ ይፋ ተደርጎአል።
በጥንት ግዜ የነገስታት መኖርያ እንደነበር እና 500 ያህል እድሜ እንደነበረዉ የሚነገረዉ የበርሊኑ ግዙፍ ቤተመንግስት በሁለተኛዉ አለም ጦርነት ሳብያ እንደ አዉሮጻዉያኑ የካቲት 3ቀን 1945 አ.ም በወደቀበት የቦንብ ናዳ ከግልጋሎት ዉጭ ቆይቶ እንደ አዉሮጻዉያኑ 1950አ.ም ቀሪዉ ህንጻ በቀድሞ የምስራቅ ጀርመን አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ እንዲፈርስ ተደርጎአል።

Deutschland Geschichte Berlin Stadtschloss Ruine
በሁለተኛ አለም ጦርነት ተጎድቶ የነበረዉ የነገስታት መኖርያ በበርሊንምስል picture-alliance / dpa

የጥንቱን የቤተ-መንግስት ቅርጽ ይዞ በዝያዉ ጥንታዊዉ ቤተ-መንግስት ቆመ በነበረበት ቦታ ላይ ሊሰራ የታቀደዉ ይህ ግዙፍ ህንጻ ጥንታዊ ቅርጹን እና ሁኔታዉን ይዞ የዘመኑን እጅግ ዘመናዊ ቁሳቁሶች እና መገልገያዎችን እንደሚያካትት ተነግሮአል።
ይህ የአለም የባህል መናኻርያ የተሰኘዉ ሙዚየም የጀርመን ነገስታት የነበራቸዉን እና ከአለም የሰበሰቡትን ባህላዊ ነገሮች የሁንቦልት ዩንቨርስቲ ቤተ-መጻህፍት እንዲሁም ባህልን በተመለከተ የምርምር ስራ የሚካሂድባቸዉ ህንጻዎችን ሲያጠቃልል እነዚህ ሶስቱ ማለት የሁንቦልት ዩንቨርስቲ ቤተ መጻህፍት፣ ጥንታዊ የጀርመን ነገስታት ባህል መጠበቅያ ድርጅት እና የባህል ምርምር ተቋም በጋራ ከአራት የባህል መናኻርያ ሙዚየሙን ህይወት ባለዉ መንገድ እንደሚያቆሙት ተገልጾአል።
የህንጻዉ ግንባታ በመጭዉ የአዉሮጻዉያኑ 2010 አ.ም ተጀምሮ እንደ አዉሮጻዉያኑ 2013 ወይም 2014 ከሶስት ከአራት አመት በኻላ ይጠናቀቃል ተብሎአል። ይህ ግዙፍ ሙዚየም 552 ሚሊዮን ይሮ እንደሚፈጅ ሲገለጽ የጀርመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ዎልፍ ጋንግ ቲፈንዜ ምንም እንኻ በወቅቱ የፋይናንስ ቀዉስ እና የኢኮኖሚ ጫና ቢኖርም ይህ የአለም የባህል መድረክ በጀርመን በርሊን እንብርት ላይ እንደሚገነባ መወሰኑን ሲገልጹ ጀርመን ባህልን የሚወድ ህዝብ ነዉ ሲሉ አክለዋል።
የጀርመን ፊደራል መንግስት 440 ሚሊዮን ይሮ ለዚሁ ግንባታ ወጪ የሚያደርግ ሲሆን የተቀረዉን ወጭ የጀርመኑ የፕሮሲሸር የባህል መጠበቅያ ተቋም እንዲሁም ከህዝብ ከሚሰበሰብ ድጎማ ለግንባታዉ ስራ ወጭ እንደሚሆን ተገልጾአል።