1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቡድን ሰባት የኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ

ሐሙስ፣ ግንቦት 27 2007

በቡድን ሰባት ጉባኤ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ከሚጠበቁት የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች አንዱ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ናቸው ። ይህንኑ በመቃወም ኢትዮጵያዉያንም እዚያ ሙኒክ ሰልፍ ወጥተዋል።

https://p.dw.com/p/1Fbun
Deutschland München Anti G7 Gipfel Proteste
ምስል Getty Images/AFP/C. Stache

[No title]

በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የ ቡድን 7 አባል ሃገራት መሪዎች የዘንድሮውን ስብስባቸውን በሚያካሂዱባት በደቡብ ጀርመን ፌደራል ክፍለ ሀገር ፤ በባቬሪያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞአቸውን መግለጻቸው ተነገረ። ጉባዔው ከሚካሄድበት ከጀርመንና ኦስትሪያ የአልፕስ ተራሮች ወሰን፤ 100 ኪሎሜትር ገደማ ራቅ ብላ በምትገኘው የክፍለ ሀገሩ ርእሰ ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ለተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ የሚቆረቆሩ፤ የአጽናፋዊውን የኤኮኖሚ ትሥሥር መርኅ የሚቃወሙ የተሰባሰቡበት ነው። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ፤ በትውልድ ሃገራቸው የሰብአዊ መብት ረገጣን በመቃወም ፤ አብረው አደባባይ የወጡ ሲሆን፣ የጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በቡድን 7 አገሮች ተጋባዥ ከሆኑ አፍሪቃውያን መሪዎች አንዱ መሆናቸውን ነቅፈዋል። በመራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አስተናጋጂነት በጉባዔው የሚሳተፉት የ 7 ቱ ታላላቅ ባለኢንዱስትሪ ሃገራት፤ የብሪታንያ ፤ ካናዳ ፤ ፈረንሳይ፣ ኢጣልያ፤ ጃፓንና ዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች ናቸው።ሸዋዬ ለገሠ ሰልፉ ከሚካሄድበት ስፍራ ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑትን በጀርመን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ አቶ ስዩም ሃብተማርያምን አነጋግራለች።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ