1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በባህር የስደተኞች ሞት እና የመብት ተሟጋቾች ጥያቄ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 2008

በተመድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት፣ በ«ዩኤንኤችሲአር» ዘገባ መሰረት፣ በሜድትሬንየን ባህር ባለፈው ቅዳሜ ወደ 500 የሚጠጉ ስደተኞች ጀልባቸው ሰምጣ ሕይወታቸው ሳያልፍ አልቀረም።

https://p.dw.com/p/1IaQN
Symbolbild Flüchtlingsboot Küste Libyen
ምስል Reuters/D. Zammit Lupi

[No title]

አምናም ተመሳሳይ አደጋ ደርሶ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስደተኞች በሞቱበት ጊዜ፣ የአውሮጳ ህብረት ይህን መሳይ አሳዛኝ አደጋ እንዳይከሰት ለማከላከል እና ወደ አህጉሩ በሕገ ወጥ የሚገቡትን ስደተኞችንም ቁጥር ለመቀነስ በሰው አሸጋጋሪዎች አንፃር ቁጥጥሩን የማጠናከር ርምጃ መውሰዱ ይታወቃል፣ ያም ቢሆን ግን ስደተኞቹ አሁንም በማያስተማምኑ ጀልባዎች በሚያደርጉት ጉዞ ሕይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ ነው። ይህ እንዳይሆን ታድያ ስደተኞች ወደ አውሮጳ በሕጋዊ መንገድ እንዲገቡ ህብረቱ ትክክለኛውን መስመር እንዲከፍትላቸው የመብት ተሟጋቾች መጠየቃቸውን ቀጥለዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ