1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአሶሳ የታሰሩ ሰዎች ቤተሰቦች አቤቱታ 

ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2012

አብዛኞቹ ታሳሪዎች አርሶ አደሮችና የመንግስት ሰራተኞች ሲሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችም እንደሚገኙበት ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል  አሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ያዕቆብ አልማሙን መረጃን በማጣራት ሂደት የተፈጠሩ ክፍተቶች መኖራቸውን አረጋግጠዋል፤የምርመራ መዝገቡ እየተጠናቀቀ መሆኑንና በቅርቡ ክስ ይመሰረታል ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3gqSy
Assosa Town Äthiopien
ምስል DW/N. Dessalegn

«ተጠርጣሪዎች ክስ ሳይመሰረትባቸው ሁለት ወር አልፏል» 


በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ከሁለት ወር በፊት ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ክስ ሳይቀርብባቸው እና ያለምንም ጥፋት ታስረው እንደሚገኙ የታሳሪ ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡ በወቅቱ በወረዳው  በነበረው ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ  ተገልጿል፡፡ አብዛኞቹ ታሳሪዎች አርሶ አደሮች እና የመንግስት ሰራተኞች ሲሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችም እንደሚገኙበት ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል  አሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ያዕቆብ አልማሙን መረጃን በማጣራት ሂደት የተፈጠሩ ክፍተቶች መኖራቸውን አረጋግጠዋል የምርመራ መዝገቡ እየተጠናቀቀ መሆኑንና በቅርቡ ክስ ይመሰረታል ብለዋል፡፡ 
ነጋሳ ደሳለኝ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ