በቤልጂየም የሽብር ጥቃት እቅድ መክሸፍ
ዓርብ፣ ጥር 8 2007ማስታወቂያ
የቤልጂየም ፖሊስ በጂሃዲስትነት የጠረጠራቸዉን ሁለት ከሶሪያ የተመለሱ መሆናቸዉ የተገለጸ ጥቃት አድራሾች ሲገድል አንዱን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተነግሯል። ፖሊስ የሽብር እቅዱን ያከሸፈዉ ከብራስልስ መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከጀርመን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘዉ የቨርቬርስ ከተማ ባካሄደዉ አሰሳ ነዉ። የቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር ፖሊስ የወሰደዉ ርምጃ መንግሥታቸዉ ሽብርን ማስፋፋት የሚሹትን ለመዋጋት መቁረጧን ያሳያል ብለዋል። ባለፈዉ ሳምንት ፓሪስ ላይ ከደረሰዉ የሽብር ጥቃት በኋላ ጀርመንን ጨምሮ አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሃገራት ከፍተኛ ጥንቃቄና ቁጥጥራቸዉን አጠናክረዋል። የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌየኋላ