1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዳንጉራ 57 ሰዎች ተገደሉ

ረቡዕ፣ ሰኔ 19 2011

የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከመካከላቸው በተኙበት በእሳት ተቃጥለው የሞቱም ይገኙበታል። የተቀሩት ደግሞ በጥይት ተመተው መገደላቸውን  17 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3L7Hn
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

በዳንጉር 57 ሰዎች ተገደሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ባንጂ በተባለ ስፍራ የታጠቁ ኃይሎች ባለፈው እሁድ አደረሱት በተባለ ጥቃት የ57 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ጃራ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከመካከላቸው በተኙበት በእሳት ተቃጥለው የሞቱም ይገኙበታል።የተቀሩት ደግሞ በጥይት ተመተው መገደላቸውን  17 ሰዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። 44 ቤቶችም መቃጠላቸውን ተናግረዋል። የአሶሳው ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ዘገባ አለው።

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ