1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤይሩቱ ፍንዳታ 10 ኢትዮጵያዉያን ሞተዋል ተባለ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 30 2012

ማክሰኞ ምሽት መዲና ቤይሩትን ባናወጠዉ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ እስካሁን 10 ኢትዮጵያዉያት መሞታቸዉ ተነገረ። በርካቶችም መጉዳታቸዉ ተነግሮአል። በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ አንዲት ኢትዮጵያዊትዋ ለዶቼ ቬለ በስልክ እንደተናገረችዉ የአገሪቱ መንግሥት እስካሁን አስር ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉን አረጋግጦአል። ለኢትዮጵያ ቆንስላም አሳዉቋል።

https://p.dw.com/p/3gYcp
Libanon | Gewaltige Explosion in Beirut
ምስል Reuters/A. Taher

 

ማክሰኞ ምሽት መዲና ቤይሩትን ባናወጠዉ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ እስካሁን 10 ኢትዮጵያዉያት መሞታቸዉ ተነገረ። በርካቶችም መጉዳታቸዉ ተነግሮአል። በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ ኢትዮጵያዊትዋ ትዕግስት ለዶቼ ቬለ በስልክ ሃሙስ ለት ከቀትር በኋላ እንደተናገረችዉ የአገሪቱ መንግሥት እስካሁን አስር ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉን አረጋግጦአል። በፍንዳታዉ እንዲሁ የቆሰሉ እንዳሉ ተናግራለች። በርግጥ እስካሁን ቁጥራቸዉ በዉል አልተጣራም ተብሎአል። በቤሩት ነዋሪ የሆነችዉ ኢትዮጵያዊት እንደናገረችዉ የሊባኖስ መንግሥት እስካሁን አስር ኢትዮጵያዉያት መሞታቸዉን ማረጋገጡን ቤይሩት ለሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽፈት ቤት አረጋግጦአል። በፍንዳታዉ ምክንያት በቤት ፍርስራሽ ዉስጥ የተቀበሩ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ባለመጠናቀቁ ምናልባትም የሟች ኢትዮጵያዉያኑ ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሎአል።

ቤይሩት የሚገኘ አሁንም በፍርስራሽ ስር የተቀበሩ አስክሪንን እያወጣች መሆኑን ተናግራለች። በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ተመስገን ዑመር ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት በሊባኖስ ከ 250 እስከ 300 ሺህ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ፤ አብዛኞቹ ደግሞ ደግሞ የሚገኙት ቤይሩት ከተማ ዉስጥ ነዉ።   

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ