1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በብሩንዲ መፈንቅለ መንግሥት ተካሄደ መባሉ

ረቡዕ፣ ግንቦት 5 2007

ጀኔራል ኒዮምባሬ ፣ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ምን ያህል ድጋፍ እንዳላቸው የታወቀ ነገር የለም። ፕሬዚዳንቱ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በመሞከር ላይ እንዳሉም ጀኔራሉ አይሮፕላን ማረፊያውና የአገሪቱ ድንበሮች ዝግ ናቸው ሲሉ ከማስታወቃቸውም እያንዳንዱ ዜጋ ይህን አዋጅ እንዲያከብር መጠየቃቸው ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1FPUo
Burundi Jubel nach dem Putsch auf den Straßen von Bujumbura
ምስል Reuters/G. Tomasevic

አንድ የቡሩንዲ ጀኔራል፣ ፕሬዚዳንት ፒየር እንኩሩንዚዛ ከሥልጣን ተፈናቅለዋል አሉ። ጀኔራል ጎድፍሯ ኒዮምባሬ፤ ኢሳንጋኒሮ በተሰኘው የግል ራዲዮ ጣቢያ በደጡት መግለጫ ፣ እንኩሩንዚዛ ከእንግዲህ በሥልጣን ላይ አይደለም የሚገኙት መንግሥታቸውም ፈርሷል ሲሉ አስታውቀዋል። ሆኖም ራሳቸው ፕሬዝዳንቱ ንኩሩንዚዛ በፌስቡክ በሰጡት መግለጫ መፈንቅለ መንግሥቱ «ከሽፏል » ብለዋል ።ረዳታቸውንም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የተባለውን እንደ ቀልድ ነው የምንቆጥረው ብለዋል ። ርእሰ ብሔር ንኩሩንዚዛ፤ በቡሩንዲ ቀውስ ሳቢያ ታንዛንያ ውስጥ ከምሥራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ መሪዎች ጋር ለመምከር ከዛሬ ጧት አንስቶ በዚያ እንደሚገኙ ነው የተገለጠው። ጀኔራል ኒዮምባሬ ፣ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ምን ያህል ድጋፍ እንዳላቸው የታወቀ ነገር የለም። ፕሬዚዳንቱ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በመሞከር ላይ እንዳሉም ጀኔራሉ አይሮፕላን ማረፊያውና የአገሪቱ ድንበሮች ዝግ ናቸው ሲሉ ከማስታወቃቸውም እያንዳንዱ ዜጋ ይህን አዋጅ እንዲያከብር መጠየቃቸው ተነገረ።
የፀጥታ መረጃ ክፍል ኀላፊ የነበሩትና ባለፈው የካቲት ከሥልጣናቸው የተነሱት ጀኔራል፤ ሕገ መንግሥቱን በሚጻረረ መልኩ፣ ለ 3ኛ ጊዜ እጩ ተወዳዳሪ እሆናለሁ ያሉትን ፕሬዚዳንት አይገባም ሲሉ ጠንከር ያለ ምክር መስጠታቸውም ሆነ መቃወማቸው ተጠቅሷል።በቡሩንዲ የፕሬዚዳንት እንኩሩዚዛን ለ 3ኛ ጊዜ እጩ ሆኖ የመቅረብ እቅድ በመቃወም፤ ብርቱ ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ 2 ሳምንት ገደማ ሆኗል።

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ