1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቦይንግ ላይ የተመሰረተው ክስ 

ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2011

ቦይንግ 737 ማክስ የተባሉት አውሮፕላኖች የአብራሪዎች የማስጠንቀቂያ ሥርዓት እንደማይሰራ ቢያውቅም ለአየር መንገዶች አለመናገሩን አመነ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲጓዙ ሕይወታቸውን ያጡ ዘጠኝ መንገደኞች ቤተሰቦች በፈረንሳይ በኩባንያው ላይ ክስ መስርተዋል።

https://p.dw.com/p/3I1Ym
Äthiopien Trauerfeier Flugzeugabsturz Boeing 737 Max
ምስል Getty Images/J. Countess

በቦይንግ ላይ የተመሰረተው ክስ 

ቦይንግ 737 ማክስ የተባሉት አውሮፕላኖች የአብራሪዎች የማስጠንቀቂያ ሥርዓት እንደማይሰራ ቢያውቅም ለአየር መንገዶች አለመናገሩን አመነ። ኩባንያው በገዛ መሐንዲሶቹ በአብራሪዎች ክፍል የተገጠመው የማስጠንቀቂያ ሥርዓት እንደማይሰራ ያወቀው በኢንዶኔዥያ የላየን አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ የ157 መንገደኞች ሕይወት ከመቅጠፉ በፊት በጎርጎሮሳዊው 2017 ዓ.ም. ነበር። 
ይኸው የአውሮፕላን አይነት በኢትዮጵያ ተከስክሶ ህይወታቸውን ያጡ ዘጠኝ መንገደኞች ቤተሰቦች በቦይንግ ላይ ፈረንሳይ ፍርድ ቤት ክስ መስርተዋል። ሐይማኖት ጥሩነሕ የከሳሾችን ጠበቃ አነጋግራ የሚከተለውን ዘገባ ልካለች። 

ሃይማኖት ጥሩነሕ
ነጋሽ መሐመድ