1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በተሽከርካሪ የተጫነዉ ቤተ-መቅደስ

ሰኞ፣ ጥቅምት 25 2000

በጀርመን የሉተራን ወንጌላዊ ቤተክርስትያን እምነት ተከታዮች በጀርመነኛዉ Reformationstag በመባል የሚታወቀዉን የእምነቱን የታህድሶ ቀን አክብረዉ ዉለዋል።

https://p.dw.com/p/E0m2
ምስል AP
የታህድሶ ቀን በመባል የሚታወቁዉ እና በየአመቱ በሉተራን ወንጌላዊት እምነት ተከታዮች የሚከበረዉ በአል እንደ አ.አ 1517 አ.ም በቅስና ሞያ ታዋቂ የነበረዉ ጀርመናዊ መነኩሴ ፕሮፊሰር ማርቲን ሉተር በእምነቱ አንድ ለዉጥ ለማምጣት አዲስ መርሆ በመቅረጹ ነበር። ይህ ማሪቲን ሉተር የዛሪ 500 አመት ያስቀመጣቸዉ መርሆዎች ተቀባይነት ቢያገኙም በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተጽኖም አሳድሮአል። በዚህም ምክንያት በወቅቱ በጀርመን በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ የእምነት መከፍፍል ማስከተሉ ይነገራል። ማርቲን ሉተር በወቅቱ በነበሩ የካቶሎክ እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ነቀፊታ እንደደረሰበት እና በርካታ ጠላችን አፍርቶ እንደነበር ጽሁፎች ይጠቁማሉ። ማርቲን ሉተር በጀርመን የፕሮቴስታንት እምነት እንዲስፋፉ ያደረገ የሉተራን ወንጌላዊት እምነት ጠንሳሽም መሆኑ ይነገርለታል። አ.አ ከ1517 አ.ም ጀምሮ በጀርመን በያመቱ ጥቅምት 20 የታህድሶ ቀን በመባል በሉተራን ወንጌላዊት እምነት ተከታዮች ዘንድ መከበር የጀመረዉ በአል የዘንድሮ አከባበር ለየት ያደረገዉ በሳክሰን ክልል Heuersdorf በምትባል የገጠር ከተማ በ12ኛዉ ክፍለ ዘመን የታነጸ የ750 አመት እድሜ ያለዉ ቤተ መቅደስ ካለበት ቦታ አስራ ሁለት ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ መወሰዱ ነበር። ይህንኑ በአል በማስከተል የቅዱሳን ቀን የተሰኘዉ በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረዉ በአል ቀንም ታስቦ ዉሎአል። በእንጎሊዘኛዉ All Saints የተሰኘዉ በአል በአዉሮፓ በሚገኙ የካቶሊክ እምነት ተከታይ አገሮች ዘንድ ይከበራል። የባህል መድረካችን ጀርመን ታስበዉ ስለ ዋሉት በአላት 12 ኪሎ ሜትር ርቀት በከባድ ተሽከርካሪ ተጮኖ ስለተወሰደዉ ቤተ መቅደስ ጉዳይ ሊያወጋጅሁ ተዘጋጅቶአል መልካም ቆይታ።