1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ በተመጣጣኝነት ይተገበራል የተባለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 26 2013

በአዋጁ ትግራይ ለመጪዎቹ 6 ወራት በወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) ትተዳደራለች። ግብረ-ኃይሉ የፀጥታ ኃይላትን በሙሉ በአንድ ዕዝ አስተባብሮ ይመራል ፣ ያዛል፤ ጥቃትን ይከለክላልም ተብላል።  

https://p.dw.com/p/3kucd
Äthiopien Parlament in Addis Abeba
ምስል DW/Y. G. Egziabher

በትግራይ ክልል እንዲደነገግ የወጣዉ የአስቸኳይ ጊዜ ደንብ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ትናንት የወጣዉን ደንብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ። የሚንስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ትናንት የደነገገዉ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን «ከአደጋ ለመከላከል» በሚል ነዉ። በአዋጁ መሠረት ከትናንት በስቲያ ሌሊቱን የፌደራል መንግስቱ ጦርና የትግራይ መስተዳድር ሚሊሺያ ወይም ልዩ ኃይላት ዉጊያ የገጠሙባት ትግራይ ለመጪዎቹ 6 ወራት በወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) ትገዛለች። ሥለ አዋጁ ይዘትና አፈፃፃም ዛሬ ዶክተር ጌድዮን ጤሞትዮስ  ለጋዜጠኞች ማብራርያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንዳሉት አዋጁን በሥራ ላይ እንዲያዉል ሥልጣን የተሰጠዉ ግብረ-ኃይል የአዋጁን ተፈፃሚነት የማጥበብ ወይም በሌሎች የሐገሪቱ ክፍሎችም ተፈፃሚ የማድረግ ሥልጣን አለዉ። ግብረ-ኃይሉ የፀጥታ ኃይላትን በሙሉ በአንድ ዕዝ አስተባብሮ በአስፈላጊነትና በተመጣጣኝነት መርህ ይተገበራል ይመራል ፣ ያዛል፤ ጥቃትን ይከለክላልም ተብላል። 

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ