1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ችግርና የነዋሪዉ ምሬት

ዓርብ፣ ጥር 6 2014

በትግራይ ክልል ለወራት ከተቋረጠ መሰረታዊ አገልግሎች ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች በከፋ ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ ። በከተሞች የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር ባልተለመደ ሁኔታ ጨምሯል፣ በልመና የሚተዳደሩ አዛውንቶችና ሴቶች ተበራክተዋል፣ ከእርዳታ አቅርቦት መስተጓጎል ጋር በተገናኘ ምክንያት በመጠልያዎች የነበሩ ተፈናቃዮች እየተበተኑ መሆኑም ተገልጿል። 

https://p.dw.com/p/45TRG
IDP’s and homeless in the city of Mekele
ምስል Million Hailesilassie/DW

በትግራይ ክልል የመጠለያ አልባነት ችግር ነዋሪውን አስመርሯል

በትግራይ ክልል ለወራት ከተቋረጠ መሰረታዊ አገልግሎች ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች በከፋ ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ ። በከተሞች የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር ባልተለመደ ሁኔታ ጨምሯል፣ በልመና የሚተዳደሩ አዛውንቶችና ሴቶች ተበራክተዋል፣ ከእርዳታ አቅርቦት መስተጓጎል ጋር በተገናኘ ምክንያት በመጠልያዎች የነበሩ ተፈናቃዮች እየተበተኑ መሆኑም ተገልጿል። 

IDP’s and homeless in the city of Mekele
ምስል Million Hailesilassie/DW

በትግራይ ላለፉት ስድስት ወራት የባንክ፣ ቴሌኮም፣ የምድርና አውሮፕላን መጓጓዣ የተቋረጠ መሆኑን እና ህዝቡ  በፋይናንስ ተቋማት ያስቀመጠውን ገንዘብ ሊያገኝ እንዳልቻለ ይገልጻል።  መድሃኒትን ጨምሮ ሌሎች የፍጆታ ሸቀጦችም ከሀገር ውስጥ ይሁን ከውጭ እንዳልገባለቸው አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። 

ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ