1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኒሻንጉል ፀጥታና የጦር መሳሪያ

ዓርብ፣ ግንቦት 16 2011

ምክር ቤቱ አዲስ በጣለዉ እገዳ መሠረት የመስተዳደሩ ሚሊሺያ፤ልዩና መደበኛ ፖሊስ አባላት የተለየ ፍቃድ ካልተሰጣቸዉ በስተቀር ተደራጅተዉም ሆነ በተናጥል ታጥቀዉ ወደ አዋሳኝ ድንበሮች የመጓዝ አይችሉም።

https://p.dw.com/p/3J2ch
Äthiopien Amharas aus Benishangul vertrieben
ምስል DW/Yohannes Gebreegziabher

የበኒ ሻንጉል ፀጥታና ጦር መሳሪያ

                 
የበኒ-ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድርን ከአማራ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች የታጠቁ ኃይላት እንዳይነቀሳቀሱ የበኒ-ሻንጉል የፀጥታ ምክር ቤት አገደ።ምክር ቤቱ አዲስ በጣለዉ እገዳ መሠረት የመስተዳደሩ ሚሊሺያ፤ልዩና መደበኛ ፖሊስ አባላት የተለየ ፍቃድ ካልተሰጣቸዉ በስተቀር ተደራጅተዉም ሆነ በተናጥል ታጥቀዉ ወደ አዋሳኝ ድንበሮች የመጓዝ አይችሉም።እገዳዉ የተጣለዉ ባለፈዉ ሚያዚያ ወር በአዋሳኝ ድንበሮች የተቀሰቀሰዉ ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳይደገም ለመከላከል ነዉ።በበኒ ሻንጉል መተከልና በአማራ ጃዊ አካባቢ በቀሰቀሰዉ ደም አፋሳሽ ግጭት በርካታ ሰዎች በግፍ ተገድለዋል፣ ከአራት ሺሕ በላይ ተፈናቅለዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋአለም ወልደየስ