1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋሙ ቀጥሏል

ዓርብ፣ ግንቦት 9 2011

በአማራ ክልል ከምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ከ70 ሺህ ተፈናቃች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወደቀያቸው መመለሳቸው እየተነገረ ነው። ተመላሾችም የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ማስተባበሪያ ኮሚሽን በሚያደርግላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን  ወደአካባቢው ሄዶ ለተመለከታቸው የባሕር ዳር ዘጋቢያችን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3Ifh3
Äthiopien RückkehrerInnen in die Region Amhara
ምስል DW/A. Mekonnen

«አብዛኞቹ ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል»

 ተፈናቃዮቹ በግጭቱ ምክንያት ከደረሰው የሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ሌላ፤ ቤት ንብረት ሰብላቸው ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸውም እንደተበተኑ በመግለፅ፤ እንዲህ ያለው ክስተት ዳግም እንዳይመጣ ሊደረግ ይገባል ያሉትንም አመልክተዋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ  ምክንያቶችና  አካባቢዎች  ግጭቶች  ተፈጥረው  በርካቶች  ለሞትና  ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፣ ሌሎች ደግሞ ቤት ንብረታቸው ተቃትሎ አካባቢቸውን እየለቀቁ ተፈናቅለዋል፡፡

በተፈጠረው ግጭት ከቀያቸው ተፈናቅለው ከነበሩት መካከል በምዕራብ ደንቢያ የጉንትር ቀበሌ ነዋሪው አቶ ስጦታው ክብረት አንዱ ሲሆኑ 90 ዚንጎ ቆርቆሮ ቤት ከነሙሉ ንብረቱ፣ 80 ኩንታል ቦቆሎ፣ 18 ኩንታል ጤፍ፣ 11 ኩንታል ዳጉሳ 4 ኩንታል ድንች፣ 2 ኩንታል ሽምብራና ሙሉ የጓሮ አትክልት በእሳት ወደወሟል፡፡

Äthiopien RückkehrerInnen in die Region Amhara
ምስል DW/A. Mekonnen

አቶ አበረ ተስፉ ሌላው ተፈናቅለው የነበሩና ወደ ቀያቸው የተመለሱ ናቸው እርሳቸውም የነበረውን ቀውስ ሲያስረዱ ከወለዷቸው ልጆች መካከል በግጭቱ ወቅት ነብሳቸውን ለማዳን  4ቱ ወደ አማራ ሲቀላቀሉ ሌሎቹ ደግሞ ወደቅማንቱ ሄደዋል ነው ያሉት። በሁለቱ ዞኖች ብቻ በተፈጠረው ችግር ምክንት 73 ሺህ ያህል የተፈናቀሉ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወደቀያቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኃላፊ አቶ አመረ ክንዴ ተናግረዋል። 

አቶ አማረ አያይዘውም እስካሁን ከሁለቱም ዞኖች  ከግማሽ በላይ ተፈናቃዮች ተመልሰዋል፣ ከ000 በላይ ቤቶችም ተገንብተዋል፡፡ አስተያየታቸውን ከሰጡኝ ተመላሾች መካከል ቤታቸው የተቃጠለባቸው የ89 ዓመቷ አማሆይ ስመኝ ወርቁ ሲሆኑ ባለ 39 ዚንጎ ቆርቆሮ ቤታቸው በሙሉ የተቃጠለ ሲሆን 45 ዚንጎ ቆርቆሮ ተሰጥቷቸው ቤታቸው በመሰራት ላይ ነወ፡፡

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ