1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለት የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከላት

ዓርብ፣ መጋቢት 27 2011

ካባሕር ዳሩ ሌላ የደሴ የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከልም ሥራ መጀመሩን የአማራ ክልል አስታውቋል። እነዚሁ በመንግሥት እና በለጋሽ ድርጅቶች ትብብር የተገነቡት ሁለት የኦክስጂን ማመረቻ ማዕከላት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣባቸው ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/3GN4i
Äthiopien Einweihung der Sauerstoffanlage in Bari Dar
ምስል DW/A. Mekonnen

የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከላት በባህርዳር እና በደሴ

መሠረታዊ መድሐኒት የሚባለው ኦክስጂን በየሆስፒታሉ በቀላሉ እንዲገኝ አቅርቦቱም ዘላቂ እና አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሠራ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በባሕር ዳር የኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል ትናንት በተመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። ካባሕር ዳሩ ሌላ የደሴ የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከልም ሥራ መጀመሩን የአማራ ክልል አስታውቋል። እነዚሁ በመንግሥት እና በለጋሽ ድርጅቶች ትብብር የተገነቡት ሁለት የኦክስጂን ማመረቻ ማዕከላት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣባቸው ተገልጿል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሀገሪቱ በኦክስጂን አቅርቦት እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ልኮልናል።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ