1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የባሕል ሳምንት እየተከበረ ነው

ሰኞ፣ ግንቦት 5 2011

በኢትዮጵያ የነበረው የመተጋገዝ፣ የመተሳሰብና የአንድነት እሴት፣ ባህልና ልምድ እተሸረሸረ በመምጣቱ በየአካባቢዎች ግጭቶች እተፈጠሩ ጉዳቶች እደረሱ መሆናቸውን በባሕር ዳር እተካሄደ ባለው የ14ኛው የአማራ ክልል የባህል ሳምንት ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3IQZP
Äthiopien Amhara Kulturfestival
ምስል DW/A. Mekonnen

በአማራ ክልል የባሕል ሳምንት እየተከበረ ነው

የአማራ ክልልን ባህልና አኗኗር የሚያሳይ የባህል ሳምንት በባህር ዳር እየተካሄደ ነው፡፡ የባህል ሳምንቱ እየተሸረሸረ ያለውንና ወደ ግጭት የሚወስደውን አለመተሳሳብና የመለያየት አባዜም ይመልሰዋል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነበረው የመተጋገዝ፣ የመተሳሰብና የአንድነት እሴት፣ ባህልና ልምድ እተሸረሸረ በመምጣቱ በየአካባቢዎች ግጭቶች እተፈጠሩ ጉዳቶች እደረሱ መሆናቸውን በባሕር ዳር እተካሄደ ባለው የ14ኛው የአማራ ክልል የባህል ሳምንት ተሳታፊዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

በባህል ሳምንቱ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል ከዋግኽምራ የመጡት አቶ እሽቱ ታደሰ እንዳሉት የእናትንና የአባትን ባህልና ልምድ ወርሶ ባግባቡ መጠቀም ባለመቻሉ ወጣቱ ለነባር እሴቶች ተገዥመሆን አልቻለም፡፡በየአካባቢው ለሚነሱ ግጭቶችም እሴቶቻችን ጠብቀን ባለመሄዳችን የመጡ ናቸውም ብለዋል፡፤ከምዕራብ ጎጃም የተወከሉት አቶ ዘለዓለም ታፈረ አንደሚሉት የአሁኑ ወጣት በምዕራባዉያን ተፅእኖ ስር መውደቁ ለነባር እሴቶች መሸርሸር ምክንያት መሆኑን ጠቁመው ይህን በትምህርት መመለስ እንደሚስፈልግ ተናግረዋል፡፡አያይዘውም የዚህ ዓይነት መድረኮች በታላላቅ ከተሞች ተወስነው መቅረት አንደሌለባቸውና ወደ ወረዳና ዞንም መውረድ አለበት ነው ያሉት፡፡
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱም የሀገራችን መልካም ባህሎችና እሴቶች እደበዘዙና በሌላ መጤ ባህል በመወረራቸው ያን የመመለስ ኃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡የተዘጋጀው የባህል ሳምንትም የክልሉና መልካም እሴቶች፣ ተውፊቶች፣ትርክቶችና መልካም ልምዶች ለመመለስ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡የባህል ሳምንቱ የተከፈተው ትናንት ሲሆን የክልልና የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር፡፡

አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ