1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአምሥት መፅሄቶችና በአንድ ጋዜጣ ላይ ክስ መመሥረቱ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 29 2006

ከመፅሄቶቹ ዋና አዘጋጆች አንዳንዶቹ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ሥራቸውን በህጉ መሠረት እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል ። ክሱን በተመለከተም ከህዝብ ጋር በቴሌቪዥን ከመስማታቸው ውጭ እስከ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድረስ ምንም ዓይነት መጥሪያ ሆነ ክስ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/1CpEG
Zeitungen Äthiopien
ምስል DW

የኢትዮጵያ ፌደራል የፍትህ ሚኒስቴር በ5መፅሄቶችና በአንድ ጋዜጣ ላይ በአቃቤ ህግ በኩል ክስ መመሥረቱን ትናንት አስታውቋል ። የፍትህ ሚኒስቴር መፅሄቶቹና ጋዜጦቹ ክስ የተመሰረተባቸው ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድና ሕዝቡ በመንግሥት ላይ አለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ በማሴር ተጠርጥረው ነው ሲል ማስታወቁን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል። ከመፅሄቶቹ ዋና አዘጋጆች አንዳንዶቹ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ሥራቸውን በህጉ መሠረት እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል ። ክሱን በተመለከተም ከህዝብ ጋር በቴሌቪዥን ከመስማታቸው ውጭ እስከ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድረስ ምንም ዓይነት መጥሪያ ሆነ ክስ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል ።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ