1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአብዬ ግዛት የተቀሰቀሰዉ አዲስ ግጭት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2005

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ሱዳን ዉስጥ በነዳጅ ዘይት በታደለዉ በአብዬ ግዛት የ21 ሰዎች ህይወት የጠፋበትን የጎሳ ግጭት ለማርገብ ሁለቱ የሱዳን ፕሪዚደንቶች መነጋገራቸዉን ገልጸዋል። የደቡብ ሱዳን ፕሪዚደንት ሳልቫኪር እና የሱዳን ፕሪዚደንት ኦማር አልበሽር ለንግግር

https://p.dw.com/p/18UH6
Die Männer des Südkordofan greifen zu Waffen um sich zu verteidigen. Foto: Cap Anamur, Undatierte Aufnahme, Eingestellt 13.02.2013
ምስል Cap Anamur

የተቀመጡት በሳምንቱ መጨረሻ አብዬ ላይ በተቀሰቀሰዉ ግጭት አንድ የተመድ ሰላም አስከባሪ ወታደር እና አንድ የጎሳ መሪ ከተገደሉ በኋላ፤ የተመድ ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን እና የአፍሪቃዉ ህብረት፤ የሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የአብዬን ጸጥታ እንዲያስጠብቁ ካሳሰቡ በኋላ ነበር። ባለፈዉ ቅዳሜ በአብዬ ስለደረሰዉ ዉዝግብ እና በአካባቢዉ ላይ መፍትሄ ስላጣዉ የጎሳ ግጭት አጠር ያለ ዘገባ ይዘናል።

09.04.2013 DW online Karte Südsudan, Juba, Joglei, Sudan eng

ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ በነዳጅ ዘይት በታደለዉ በሰሜን እና በደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ በተቀሰቀሰዉ ግጭት ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸዉን፤ ከሟቾቹ መካከል አንድ የጎሳ መሪ ፤ እንዲሁም በተ,መ ሰላም አስከባሪ ስር የሚገኝ የኢትዮጵያ ወታደር እንደሚገኝበት የሱዳን እና የተመድ አስተዉቀዋል። ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ባለፈዉ መጋቢት ወር ድንበር አቋረጭ የነዳጅ ዘይት ንግዳቸውን መለሶ ለማንቀሳቀስና ውጥረትን ለማለዘብ ቢስማሙም በአብዬይ ባለቤትነት ጉዳይ ግን ከአንዳች ውሣኔ ሳይደርሱ መቅረታቸው ይታወቃል። በነዳጅ ሃብት በታደለው አካባቢ ዲንካና ምሥሪያ የተሰኙት ለደቡቡና ለሰሜኑ ክፍል ያደሉ ጎሣዎች ለባለቤትነት ሲወዛገቡ ቆይተዋል። በሱዳን የቀድሞ የተመድ ልዑካን ተጠሪ ፔተር ሹማን ሁለቱ ሱዳኖች ይላሉ

«እንደሚመስለኝ ይህ ሊከሰት የማይገባ የነበረ አደጋ እንደገና የሚያሳየን ስምምነቱ የተደረሰዉ በማዕከላዊ ደረጃ በካርቱም እና በጁባ መካከል መሆኑን እና፤ ስምምነቱን ግን በርግጥም የአካባቢዉ ህብረተሰብ እንዳልተረዳዉ እና ተቀባይነት እንዳላገኘ ነዉ። በሌላ በኩል ዩኒሳ የተሰኘዉ የተመ ሰላም አስከባሪ ሃይል ቦታ ላይ ነበር፤ቢሆንም ግን ይህን አደጋ መከላከል አልተቻለም። እንደሚመስለኝ እዚህ ላይ የሁለት ነገሮች ቅንጅት አለ። በማዕከላዊ ደረጃ የተደረሰዉ ስምምነት እና የዉጭ ሃይላት ሁኔታዉን መቆጣጠር አለመቻላቸዉ። ስለዚህ ምንም እንኳ ሳልቫኪር እና ኦማር አልበሽር ስምምነት ላይ ቢደርሱም ስምነቱ በቀጣይ አካባቢዉ ላይ ተቀባይነት እንዲኖረዉ ለማድረግ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል»በሳምንቱ መጨረሻ በነዳጅ ሃብት በታደለችዉ በአብዬ ግዛት በተነሳዉ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸዉን፤ ከሟቾቹ መካከል ከጎረቤት ሱዳን የሚገኘዉ NGOK DINKA ጎሳ መሪ ሁለት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች እና 17 የምሥሪያጎሳ አባላት መሆናቸዉን የሱዳኑ የሀገር ዉስጥ ሚኒስቴር በአገሪቱ ብዙሃን መገናኛ መግለፃቸዉ ተዘግቦአል። በአብዬ የሚገኙት ምሥሪያጎሳ ሚሊሽያዎች እነማን ናቸዉ፤ የጥቃቱ አላማስ ምንድን ነዉ?ፔተር ሹማን «ምሥሪያበአካባቢዉ ላይ የታወቁ እና በአርብቶ አደርነት የሚተዳደሩ ናቸዉ። አካባቢዉንም ለአስርተ ዓመታት ተቆጣጥረዉ ይገኛሉ። ከረጅም ዓመታት በፊት ከNGOK DINKA ጎሳ መሪቱን እንዲገለገሉበት፤ ዉሃዉን እንዲጠቀሙ ስምምነት ደርሰዋል። በኋላ የሱዳን መንግስት በጦርነቱ ወቅት የሚዜርያ ጎሳን በፊት አዉራሪ ጦር፤ በሚሊሽያነት እያዘመተ ተጠቅሞባቸዋል። ስለዚህ እንደሚመስለኝ ምሥሪያጎሳ በባህሉ ጦረኛ በሌላ በኩል ለፖለቲካ እና ለፀጥታ ሁኔታ ቁጥጥር ጥቅም ላይ የዋለ ጎሳ ነዉ።»

የአብዬን ግዛት ጨጥታ ለማስጠበቅ በተመጦር ሃይል «UNISFA« ስር ወደ 4000 የኢትዮጵያ ወታደሮች መኖራቸዉ ይታወቃል። «UNISFA» ማለት በአብዬ የሚገኘዉ የተመ ሰላም አስከባሪ ጦር የአካባቢዉ ጸጥታ በማስጠበቁ ረገድ በተለይ ከወታደር ነጻ የሆነዉን አካባቢ ከጦር መሳርያ ነጻ በማድረጉ ረገድ ምን ያህል ሚናን ይጫወታል? በሰሜን ሱዳን የቀድሞ የተመድ ሚሽን ተጠሪ ፔተር ሹማን ፤ የኔ ወቀሳ እና ትችት ይላሉ ሱዳኖች ይላሉ

Sudan's President Omar Hassan al-Bashir (L) and his South Sudan counterpart Salva Kiir listen to their national anthems upon his arrival at the Juba Airport in South Sudan April 12, 2013. Bashir visits South Sudan on Friday for the first time since Africa's once-largest country split in 2011, raising hope the two long-time adversaries will take steps to establish peaceful co-existence. REUTERS/Andreea Campeanu (SOUTH SUDAN - Tags: POLITICS)
ምስል Reuters

« የኔ ዋና ወቀሳ እና ትችት «UNISFA» በአካባቢዉ ላይ ስላለዉ ተግባር ነዉ። በተደጋጋሚ እንዳየነዉ የተመ አብዬን እንደሚቆጣጠር ማሳየቱ ነዉ ምንም እንኳ በአብዩ ዉስጥ ባይሆንም ቅሉ። የተመ በአብዬ የሚገኘዉን የሲቪል ማህበረሰብ ለመጠበቅ፤ ግጭቶችን ለማስወገድ ስምምነቶችን መድረስ እርዳታ የመስጠት፤ ችግሮችን ለመፍታት ጠልቆ የማይገባ ሃይል በማቅረብ ረጅም ስራ ያለዉ ነዉ---። እናም ይህ ጦር ሃይል ባለበት ሁኔታ ይህ አይነት አደጋ መድረሱ እኔ እስካሁን ልረዳዉ ያልቻልኩት ጉዳይ ነዉ።»

ደቡብ ሱዳን በአብዬ ግዛት የ NGOK DINKA ጎሳ መሪ DENG Majokን ማን እንደገደለ UNISAF ማጣራት እንዳለበት እና ለፍርድ መቅረብ እንዳለበት ጠይቃለች። የሱዳን ወታደሮች ከዓመታት ይዞታ በኋላ ባለፈዉ ግንቦት አካባቢዉን ለቀዉ ከወጡ ወዲህ ባለፈዉ ሳምንት ቅዳሜ አብዬ ላይ የደረሰዉ ግጭት የመጀመርያዉ መሆኑ ነዉ። ሱዳን በወታደራዊ ሃይል አብዬን ከወረረች ወዲህ 100,000 ያህል ህዝብ አብዬን በመልቀቅ ወደ ደቡብ ሱዳን መፍለሱ ይታወቃል።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ