1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲሱ ጠ/ሚ ላይ የተጣለው ተስፋ እና ተግዳሮት

እሑድ፣ ሚያዝያ 21 2010

ከሁለት ዓመት በላይ በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ የሕዝብ አመፅ ስትናጥ የከረመችው ኢትዮጵያ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተሰየመላት ጥቂት ሳምንታት ተቆጠሩ። አንደተ ርቱዑ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከበዓለ ሲመታቸው አንስተው በሚያደርጓቸው ንግግሮች የሕዝቡን ቀልብ መግዛቱ ተሳክቶላቸዋል።

https://p.dw.com/p/2wocc
Dr. Abiy Ahmed
ምስል DW/S. Teshome

ተስፋና ተግዳሮት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ

በድፍኑ ተቀባይነት ያገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር በበርካታ ችግሮች ለተወጠረችው ሀገር ፤ እንዲሁም መሠረታዊ ጥያቄዎችን መጠየቁን ላላቋረጠው ሕዝብ የሚሻዉን ለውጥ እንዲያሳዩ ይጠበቃሉ። የተሸከሙትን ኃላፊነት ሰከን ብለው የተረዱ ዶክተር ዐቢይ ለሕዝብ የሰጡትን ቃል በተግባር ለማሳየት ጊዜም ሆነ ትብብር ያስፈልጋቸዋል ይላሉ። ቃላቸው ተስፋ የዘራበት ወገን በበኩሉ ጥያቄውን ይዞን እንቅስቃሴያቸውን በንቃት መከታተሉን ተያይዞታል። ዶቼ ቬለ በአዲሱ ጠ/ሚ ላይ የተጣለውን ተስፋ እና ተግዳሮቶችን የዳሰሰበት ዉይይት አካሂዷል።

ሙሉ ውይይቱን ከታች ከሚገኘው የድምፅ ዘገባ ማዳመጥ ይቻላል።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ