1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት አሌፖ ውስጥ ቢያንስ 39 ሰዎች ተገደሉ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 7 2009

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በምትገኘው አሌፖ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት በዛሬው ዕለት ቢያንስ 24 ሰዎች መገደላቸውን የሶርያ ሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ ቡድን ገለጠ። የሶርያ መንግስት ቴሌቭዥን ጣቢያ ጥቃቱ በ«አሸባሪ ቡድኖች» ተፈፅሟል ብሏል። የቴሌቭዥን ጣቢያው 39 ሰዎች መገደላቸውን ገልጧል።

https://p.dw.com/p/2bI0T
Mindestens 16 Tote bei Bombenanschlag auf Busse in Syrien
ምስል Reuters

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በምትገኘው አሌፖ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት በዛሬው ዕለት ቢያንስ 24 ሰዎች መገደላቸውን የሶርያ ሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ ቡድን ገለጠ። የሶርያ መንግስት ቴሌቭዥን ጣቢያ ጥቃቱ በ«አሸባሪ ቡድኖች» ተፈፅሟል ብሏል። የቴሌቭዥን ጣቢያው 39 ሰዎች መገደላቸውን ገልጧል። በሰሜን ምዕራባዊ ሶሪያ በአማጺያን ቁጥጥር ስር ከሚገኙት ፉዓ እና ካፍራያ ከተባሉ ከተሞች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመውጣት አሌፖ ውስጥ እንደተከማቹ ነበር ጥቃቱ የደረሰው ሲል ታዛቢ ቡድኑ አስታውቋል።

አጥፍቶ ጠፊው አል ረሺድ በተባለው ሥፍራ የርዳታ ቁሳቁሶች መጫን የነበረበትን ተሽከርካሪ ከከተሞቹ ለመውጣት የተዘጋጁ ዜጎች ከጫኑ አውቶቡሶች ጋር በማጋጨት ቦምብ ማንጎዱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። በጥቃቱ በርካታ ሰዎች በመቁሰላቸው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሏል።ጥቃቱ ሲፈጸም ከፉዓ እና ካፍራያ የወጡት ዜጎች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ወደ ምትገኘው አሌፖ ተጉዘው ወደ ላታኪያ አሊያም ደማስቆ ሊያመሩ ነበር ተብሏል።

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ