1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፋርና ሶማሌ ግጭት 100 ያክል ሰዎች ተገደሉ

ረቡዕ፣ መጋቢት 29 2013

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የብልፅግና አባላትና መሪዎች የሆኑት የአፋርና የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት ከጂግጂጋና ሰመራ በቃላት ከመቆራቆስ ባለፍ በድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ የገጠሙትን ዉዝግብ በድርድር መፍታት አልቻሉም።ወይም አልፈለጉም።

https://p.dw.com/p/3rgtp
Äthiopien Afar trockene Landschaft
ምስል DW/G. Tedla

የአፋርና የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት እየተወቃቀሱ ነዉ

የአፋል ክልልን ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ካለፈዉ ሳምንት አርብ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት 100 ያክል ሰዎች መገደላቸዉ ተነገረ። የሁለቱ ክልልሎች ባለስልጣናት ለግጭቱ መቀስቀስ አንዳቸዉ ሌላቸዉን ይወነጅላሉ።ባለስልጣናቱ በየፊናቸዉ እንደሚሉት ግጭቱ የሁለቱን ክልልሎች ልዩ የፖሊስ ኃይል ያሳተፈና በየክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚመራ ነዉ።የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የብልፅግና አባላትና መሪዎች የሆኑት የአፋርና የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት ከጂግጂጋና ሰመራ በቃላት ከመቆራቆስ ባለፍ በድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ የገጠሙትን ዉዝግብ በድርድር መፍታት አልቻሉም።ወይም አልፈለጉም።

 መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ