1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኡጋንዳ ዳግመኛ አመጽ መቀስቀስ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 9 1999

በኡጋንዳ መንግስት እና የጌታ ተከላካይ ጦር ተብሎ በሚጠራዉ አማፂ ቡድን መካከል የፊታችን ቅዳሜ ሊደረግ የታቀደዉ የሰላም ዉል አደጋ ላይ ወድቋል

https://p.dw.com/p/E0hu
ፕሬዝደንት ዩቬሪ ሙሴቪኒ
ፕሬዝደንት ዩቬሪ ሙሴቪኒምስል dpa


የአገሪቷ ነጻ ጋዜጦች እንደዘገቡት የአማፂዉ ቡድን እና፣ መንግስት ባለፈዉ ነሃሴ ያደረጉትን የተኩስ አቁም ስምነት አፍርሰዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተለይ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከባድ የተኩስ ልዉዉጥ በመደረጉ ዉጥረቱ እያየለ ነዉ። ይሁን እና የኡጋንዳ ፕሪዚደንት Yoweri Museveni በሳምንቱ መጨረሻ በደቡብ ሱዳን ጁባ ሊደረግ በታሰበዉ የሰላም ስምምነት ስነ ስርአት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ከሃያ አመታት በላይ የቆየዉ የኡጋንዳዉ ጦርነት፣ ከአስር ሺህ ህዝብ በላይ አልቋል ሁለት ሚሊዮን ህዝብ ተፈናቅለዋል። የኡጋንዳ መንግስትም ሆነ የየጌታ ተከላካይ ጦሩ Lordś resistance army ባለፈዉ ነሃሴ ወር የተኩስ አቁም ስምምነት የገቡትን ዉል አፍርሰዉ ከሁለቱም ወገን የተኩስ ልዉዉጥ መሰማት ከጀመረ ሳምንት አስቆጥሮአል።

የፊታችን ቅዳሜ 21.10.06 ደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ዉስጥ የኡጋንዳ መንግስት እና አማጺዉ፣ በአገሪቷ ሰላም ለማስፈን በጠረቤዛ ዙርያ ለመቀመጥ ወስነዋል። ጋብ ብሎ የከረመዉ የኡጋንዳዉ የእርስ በርስ ጦርነት በሰላም ድርድሩ ዋዜማ የመቀስቀሱ ምንጭ ከኡጋንዳ መንግስት እንደሆነ የLordś resistance army ሲከስ በተጨማሪም ህዝቡ ከመንግስት ጦር ግፍ ይደርስበታል ይላል። በትናንትናዉ እለት18.10.06 የጌታ ተከላካይ ጦር ብሎ እራሱን የሚጠራዉ አማጺ ቡድን በአደረገዉ የአጸፋ ተኩስ አንድ የመንግስት መከላከያ መኮንን ተገሏል። በኡጋንዳ ዉጥረቱ እና ግጭቱ እየጨመረ ቢሄድም ፕሪዚዳንት Yoweri Museveni በአገራቸዉ የሰላም ማስፈኑ ሂደት ስኬት ደስተኛ ናቸዉ። Museveni በትናንትናዉ እለት ለቢቢሲ የዜና ወኪል በሰጡት ቃለምልስ አማጽያኑ አገሪቷን በመለቅ ወደሌሎች አገር ተሰደዋል ባይ ናቸዉ...
«ኡጋንዳን በሚመለከት፣ በአገሪቷ በሰላሙ ድርድርም ሆነ ያለ ድርድር ጸጥታን ማንገስ አለብን። በኡጋንዳ ጸጥታን ለማንገስ የሰላም ድርድር ለማድረግ ዉሳኔ ላይም ደርሰናል። ከዚያም ነዉ፣ ገና የሰላም ድርድሩ ሳይጀምር አማጺዎች ወደ ኮንጎ የፈለሱት። ቢሆንም ግን በሰሜናዊቷ ኡጋንዳ አንዳንድ ተሸሽገዉ የሚገኙ የአማጺ መሪዎችም አሉ፣ እያደናቸዉ ነዉ። ግን ሰላም ለማንገስ የሚደራደሩ ከሆነ በትክክል ልናነጋግራቸዉ ዝግጁነን፣ በዚህም ምክንያት በአገሪቷ በአፋጣኝ ሰላም ይገኛል ማለት ነዉ። ክፋቱ ግን አብዣናዎቹ አማጺዎች ወደ ኮንጎ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ ደቡብዊ ሱዳን ፈርጥጠዋል፣ ኢዝያ እንደ አንድ ስደተኛ ቢቀመጡ የአለም አቀፉ ህብረተሰብ፣ የሱዳን እና የኮንጎ መንግስት ችግር ነዉ የሚሆን፣ ወደዚህ ድጋሚ ቢመጡ ደግሞ ይታደናሉ»

ሙሴቪኒ አሁን በተነሳዉ ግጭት ምክንያት የተደናቀፈዉ የተኩስ አቁም ስምምነት፣ ለመምከር እና በአሪቷ ሰላም ለማስፈን በሳምንቱ መጨረሻ በደቡብ ሱዳን፣ ጁባ እንደገና በሚደረገዉ የሰላም ስምነት ላይ እንደሚገኙ በርግጠኝነት ገልጸዋል። ሙሴቪኒ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የአስታራቂነቱን ቦታ የሚይዙትን የሱዳኑን ምክትል ፕሪዚደንት Salva Kiir በግል እንደሚያገኙዋቸዉም ታዉቋል። ሁለት አስርተ አመታትን ያስቆጠረዉ የርስ በርስ ጦርነት አብቅቶ ባለፈዉ ነሃሴ በኡጋንዳዉ መንግስት እና በጌታ ተከላካይ ጦሩ (Lordś resistance army) መካከል የተደረሰዉ የተኩስ አቁም ስምምነት የተጣሰበት ድርጊት ሁለቱም ወገኖች የግጭቱ መነሻ እንደሆኑ ይወቃቀሳሉ። በአሁኑ ወቅት በደቡባዊ ሱዳን እና በዲሞክራቲክ ኮንጎ አዋሳኝ በሁለቱም ወገኖች መካከል የቀን ተቀኑ ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የአማጺዉም ሆነ የመንግስቱ ጦር እንዴት እና ማን የዚህ ግጭት አነሳሽ እንሆነ በግልጽ ያቁታል። ቀሪዉ አለም ደግሞ ይህን ከሃያ አመታት በላይ የፈጀ ጦርነት የማቆም ፍላጎት እንዳላቸዉ በመጠየቅ ላይ ነዉ። ያም ሆነ ይህ፣ የአማጽያኑ ቡድን ማንነታችን ከተጋለጠ፣ እንታሰራለን ከዚያም አልፎ አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ፊት እንቆማለን፣ የሚል ስጋት አለባቸዉ። የኡጋንዳም ወታደር አማጽያኑን ለመዋጋት ከአለም አቀፍ ለጋሾች ድጋፍን ያገኛሉ።
አዜብ ታደሰ