1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ሽምግልና የሱዳን ም/ቤትና የተቃዋሚዉች ስምምነት

ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2011

በሱዳን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማህሙድ ድሪር የሱዳን ተቃዋሚዎች ከእሁድ ጀምሮ ሲያካሂዱ የቆዩትን የሲቢል እምቢተኝነት ለማቆም በተስማሙት መሠረት ዛሬ ህዝቡ ወደ እለት ተለት ሥራው መመለሱን አስታወቁ። ተቃዋሚዎች በየቦታው ያቆሙዋቸን መሰናክሎችንም እያነሱ መሆኑን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3KIGa
Sudan Khartoum Vermittlung von äthiopischen Botschafter Mohamoud Dirir
ምስል Ethiopian Embassy Khartoum

ዛሬ ሱቆች መከፈት መጀመራቸው ተነግሯል

በሱዳን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማህሙድ ድሪር የሱዳን ተቃዋሚዎች ከእሁድ ጀምሮ ሲያካሂዱ የቆዩትን የሲቢል እምቢተኝነት ለማቆም በተስማሙት መሠረት ዛሬ ህዝቡ ወደ እለት ተለት ሥራው መመለሱን አስታወቁ። የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት እና ተቃዋሚዎችን ሲሸመግሉ የቆዩት አምባሳደር ማህሙድ ድሪር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤትም የያዛቸውን የፖለቲካ እስረኞች ለመልቀቅ መስማማቱን ተናግረዋል።ወታደራዊው የሽግግሩ ምክር ቤት መሪዎች እና የሱዳን ተቃዋሚዎች ከዚህ ቀደም የጀመሩትን ንግግር በቅርቡ ለመቀጠልም ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ሁለቱን ወገኖች በተናጠል በማነጋገር የሸመገሉት አምባሳደር ማህሙድ ድሪር አስታውቀዋል። ተቃዋሚዎች በየቦታው ያቆሙዋቸን መሰናክሎችንም እያነሱ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ሁለቱን ወገኖች ለመሸምገል ሱዳን ደርሰው ከተመለሱ በኋላ የሽምግልናውን ሥራ የቀጠሉት አምባሳደር ማህሙድ ድሪር እንዳሉት ሽምግልናው እልህ አስጨራሽ የነበር።በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደርና ልዩ መልክተኛ መሐመድ ድሪርን አዜብ ታደሰ አነጋግራቸዋለች ።

Sudan Khartoum Vermittlung von äthiopischen Botschafter Mohamoud Dirir
ምስል Ethiopian Embassy Khartoum

አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሃመድ