1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ቱሪዝም ላይ ጦርነት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያጠላው ጥላ

ማክሰኞ፣ መስከረም 18 2014

ባለፈው አንድ ዓመት ኢትዮጵያ ላይ ባጠላው የኮቪድ-19 ዓለማቀፍ ወረርሽኝ እና  ጦርነት ሳቢያ አገሪቱ ቢያንስ ከአንድ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማጣቷ ተገለጸ፡፡ የመሰረታዊ አገልግሎቶች አለመሟላት የሚፈትነው የኢትዮጵያ ቱሪዝም  በአሁን ወቅት ከፍተኛ ትኩረት ይሰብ የነበረው በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ባለው የሰላም እጦት መደናቀፉ ተገልጿል ፡፡

https://p.dw.com/p/40zgD
Äthiopien Tourismus Potential
ምስል Seyoum Getu/DW

በኢትዮጵያ ቱሪዝም ላይ ጥርነት እና የኮቪድ 19 ወረርሽን ያጠላው ጥላ

ባለፈው አንድ ዓመት ኢትዮጵያ ላይ ባጠላው የኮቪድ-19 ዓለማቀፍ ወረርሽኝ እና  ጦርነት ሳቢያ አገሪቱ ቢያንስ ከአንድ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማጣቷ ተገለጸ፡፡

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስከያጅ አቶ ስለሺ ግርማ በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት የመሰረታዊ አገልግሎቶች አለመሟላት የሚፈትነው የኢትዮጵያ ቱሪዝም በተለይ በአሁን ወቅት ከፍተኛ ትኩረት ይሰብ የነበረው በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ባለው የሰላም እጦት ተደናቅፏል ፡፡

ይህ ደግሞ ኑሮአቸውን በቱሪዝም ይመሩ የነበሩትን ዜጎች ህይወት አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል፡፡

ኢንደስትሪውን በኢትዮጵያ ለማዘመን እና ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎችም በነዚህ ፈተና ጥያቄ ውስጥ ወድቋል ባይ ናቸው ኃላፊው፡፡

ስዩም ጌቱ 

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ