1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ነፃ የጋዜጠኞች ምክር ቤት ምሥረታ ጥያቄ

ሰኞ፣ ሰኔ 16 2006

የጋዜጠኝነትን ሙያ የሚያስከብሩ ነፃ ጋዜጠኞች የሚመሩት ማህበር መቋቋም ለሙያው እድገትም ሆነ ለጋዜጠኞች ደህንነት ወሳኝ መሆኑን ተናግሯል ።

https://p.dw.com/p/1COYy
Ethiopian Journalists Forum
ምስል DW/G. Tedla

ኢትዮጵያ ውስጥ ከመንግሥትም ከተቃዋሚዎች ነፃ የሆነ የጋዜጠኞች ምክር ቤት እንዲቋቋም ተጠየቀ ። የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ የፕሬስ ነፃነትና የጋዜጠኞች ደህንነትና ልማት በሚል ርዕስ በካሄደው ውይይት ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች የጋዜጠኝነትን ሙያ የሚያስከብሩ ነፃ ጋዜጠኞች የሚመሩት ማህበር መቋቋም ለሙያው እድገትም ሆነ ለጋዜጠኞች ደህንነት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ። ጋዜጠኞች በሚታሰሩባት በኢትዮጵያ በፍራቻ ምክንያት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጋዜጦች ቁጥር እያነሰ በመሄድ ላይ መሆኑንም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል ። ውይይቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላች ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ